በተጠረጠሩበት የነፍስ ግድያ መርማሪዎችና ዓቃቤ ሕግ መመሳጠራቸው ተጠቆመ

የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ ወንድሙ ቢራቱን በተጠረጠሩበት ከባድ የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ሥር አውሎ እየመረመራቸው የሚገኘው የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን፣ ሰሞኑን ባካሄደው

ምርመራ ተጠርጣሪው ከግለሰቦች 10.5 ሚሊዮን ብር ጉቦ የተቀበሉበትን ሰነድ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡

መርማሪ ቡድኑ ከግለሰቦች ጉቦ ለመቀበላቸው የምስክሮችን ቃል መውሰዱን አክሏል፡፡ ተጠርጣሪው በሕገወጥ መንገድ ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪዎችን በሌሎች ግለሰቦች ስም ማስገባታቸውን የጠቆመው መርማሪ ቡድኑ፣ ተሽከርካሪዎቹን ማሳገዱን አስረድቷል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ በድን ባለፉት ሳምንታት ባካሄደው ምርመራ፣ ተጠርጣሪው በተጠረጠሩበት የነፍስ ግድያ ወንጀል በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖችና በአዲስ አበባ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን መሰብሰቡን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ አቶ ወንድሙ በነፍስ ግድያ ተጠርጥረው እያለ፣ መርማሪዎችና ዓቃቤ ሕግ ተመሳጥረው ወደ ምስክርነት እንዲዛወሩ ማድረጋቸውንም የሚያስገነዝብ ማስረጃ መሰብሰቡን ገልጿል፡፡

ቀደም ብሎ እንደሚያከናውናቸው ከገለጻቸው የምርመራ ሥራዎች ውስጥ በተጠርጣሪው ላይ በጉምሩክ ተጀምሮ የነበረውንና በመመሳጠር ተቋርጦ የነበረውን ጅምር የምርመራ መዝገብ ከጉምሩክ መቀበሉንም ገልጿል፡፡ ሐሰተኛ ሰነድ እያሳተሙ በተለያዩ ከተሞች ሲፈጽሙ የነበረውን ግብር የመሰብሰብ ድርጊት የሚያስረዱ ምስክሮችን እያፈላለገ እንደሚገኝ መርማሪ ቡድኑ ገልጿል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን ጨምሮ እንደገለጸው፣ ለተጠርጣሪው ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግሥት ግብርን እንዲሰበስቡ ደረሰኝ አትሞ ከሰጣቸው ግለሰብ የምስክርነት ቃል መቀበል ይቀረዋል፡፡ ሌሎች ለመንግሥት መግባት የነበረባቸውን የተጨማሪ እሴት ታክስና ግብር ለማስቀረት ጉቦ የተቀበሉበትን የባንክ ሰነድ መሰብሰብና ተጨማሪ የሰው ማስረጃ መሰብሰብ ይቀረዋል፡፡ 

ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሰው ማስረጃ ቃል መቀበሉን፣ ተጨማሪ የሰነድ ማስረጃ መሰብሰብ እንደሚቀረውና ሎሎች ተፈላጊ ተጠርጣሪዎችን አድኖ መያዝ እንዳለበት ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ጉቦ ሲቀበሉና ሲያቀብሉ የነበሩበት የባንክና ሌሎች ሰነዶችን ከመጠቀም በተጨማሪ፣ በሥልጣን ዘመናቸው ሲያጠራቅሙ የነበረውን ተጨማሪ የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ሀብት ማፈላለግ እንደሚቀረው ለፍርድ ቤቱ ገልጾ፣ ይኼንን ለሚያከናውንበት ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲፈቀዱለት ጠይቋል፡፡

የተጠርጣሪው ጠበቃ መርማሪ ቡድኑ ያቀረበውን ተጨማሪ ጊዜ በመቃወም፣ እስካሁን ያደረገው ምርመራ በቂ መሆኑንና ተጨማሪ ምርመራ እንደማያስፈልግ በማስረዳት፣ የደንበኛቸው የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸውና ከእስር እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ግን ቀሪ ምርመራ እንደሚቀረው ማስረዳቱን በማስታወስ ዋስትናውን ተቃውሟል፡፡

ተረኛ ችሎቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ፣ የተጠርጣሪውን ጠበቃ አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ለመርማሪ ቡድኑ የሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል፡፡ 

 

ምኒሊክ ሳልሳዊ = በሕወሓት ተመልምለው ከውጪው አለም የሚኖሩ ዲያስፖራ የሕወሓት ደጋፊዎች የደህንነት እና ስለላ ስራዎችን ስልጠና በጦላይ ከጨረሱ በኋላ ወደየመጡበት አህጉር መመለሳቸው ምንጮች ጠቁመዋል::ከሰሜን አሜሪካ አውሮፓ እና መካከለኛ ምስራቅ እንዲሁም ከአፍሪካ ተመልምለው የመጡ እና በስራ ፈትነት በዲያስፖራው መሃል ሲኖሩ የነበሩ …

በጦላይ የሰለጠኑ የሕወሓት ደህንነቶች ወደየመጡበት አህጉር ተላኩ:: Read more »

ድምፃችን ይሰማ . ሁላችንም ለስኬታማነቱ በብር ላይ በመፃፍ እንረባረብ! . ባለፉት ጥቂት የትግል አመታት ከህዝብ ወደ ህዝብ በሚሰነዘሩ የተለያዩ ሐሳቦች በመገፋት የቀጠለው ሰላማዊ ትግላችን በሂደት ጥቂት የማይባሉ የሰላማዊ ትግል ስልቶችን ተጠቅሞ ድምጹን ለማሰማትና የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ ድርጊቶችም እንዲቆሙ ለማስደረግ ሲጥር …

የድምጻችን ይሰማ ‹‹የወረቀት ብር ግራፊቲ›› (Money Grafitti)ተግባራዊ ስራ ተጀመረ:: Read more »

በሳዑዲው አሰቃቂ አደጋ የአገሪቱ ባለሥልጣናት እየተወዛገቡ ነው

131 ዜጎቿን ያጣችው ኢራን፤ ሳኡዲ አረቢያን ተጠያቂ አድርጋለች
እስካሁን በአደጋው 717 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል

በሳዑዲ አረቢያ በሀጂ ስነስርዓት ላይ ከትናንት በስቲያ 717 ሰዎች በሞቱበት አደጋ የአገሪቱ ባለስልጣናት እየተወዛገቡ ሲሆን፤ የኢራን መንግስት 131 ዜጐቹ መሞታቸውን በመግለጽ የሳዑዲን መንግስት ተጠያቂ አድርጓል፡፡
ከመካ በ5 ኪ.ሜትር ርቀት በሚገኘው ሚና የሚባል አካባቢ፣ በሰይጣን ላይ ድንጋይ የመወርወር ሃይማኖታዊ ስነ ስርአት ላይ በተፈጠረ ግርግር ነው አደጋው የተከሰተው ተብሏል፡፡ የብዙዎችን ህይወት በቀጠፈው አደጋ፤ 863 ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ለሃጂ ስነስርዓት በሄዱ ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰ አደጋ ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም፡፡
የኢራን መንግስት መሪ አያቶላ ሆሚኒ፤ አደጋው የተፈጠረው በሳዑዲ መንግስት ዝርክርክ አሰራር ነው፤ ለአደጋው ሙሉ ኃላፊነቱን መውሰድ አለበት ብለዋል፡፡
የሳኡዲ የጤና ሚኒስትር ካሊድ አል-ፍሌህ በዚህ አይስማሙም፡፡ አደጋው የተከሰተው በምዕመናን ጥፋት ነው ብለዋል፡፡ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መንሱር አልቱርኪ፤ ተመሳሳይ ሃሳብ ሰንዝረዋል፡፡ ብዙ ምዕመናን፤ በተመሳሳይ ሰአት በጠባብ መተላለፊያ ላይ የፈጠሩት ግርግር የአደጋው መንስኤ ነው ብለዋል – ቃል አቀባዩ፡፡
የሀጂ ኮሚቴ ሊቀመንበር ልዑል መሃመድ ቢን ናይፍ በበኩላቸው፤ የአደጋው መንስኤ በአስቸኳይ ተጣርቶ እንዲቀርብላቸው ትዕዛዝ የሰጡ ሲሆን፣ የሀገሪቱ ንጉስ ሰልማን ግን የሀጂ ጉዳይ ድርጅቱ እንደገና እንዲዋቀር አዘዋል፡፡
በአደጋው ከሞቱት መካከል፣ 131 የኢራን፣ 14 የህንድ፣ 18 የቱርክ፣ 7 የፓኪስታን፤ 3 የአልጄሪያ እና 3 የኢንዶኔዢያ ዜጎችን ጨምሮ፣ ቁጥራቸው ያልተጠቀሰ የናይጄሪያ፣ ኒጀር፣ ቻድ፣ እና ሴኔጋል ዜጎች የአደጋው ሰለባ ሆነዋል ተብሏል፡፡
በሳኡዲ የብዙዎችን ህይወት የቀጠፈ አደጋ በአንድ ወር ውስጥ ሲያጋጥም ያሁኑ ሁለተኛው ነው፡፡ ከቀናት በፊት በመካ ታላቁ መስጊድ ላይ፤ የግንባታ ክሬን ወድቆ፣ 109 ሰዎች መሞታቸው ይታወቃል፡፡
ከትናንት በስቲያ ያጋጠመው አደጋ ከተሰማ በኋላ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ባንኪሙን እና የካቶሊክ ፓፓስ ፍራንሲስ የሀዘን መልዕክታቸው ካስተላለፉት ቀዳሚዎቹ ሆነዋል፡፡
እ.ኤ.አ በ1990 ካጋጠመውና 1426 ሰዎችን ለህልፈት ከዳረገው ተመሳሳይ አደጋ ቀጥሎ የሰሞኑ የበርካታ ምዕመን ህይወት የተቀጠፈበት አደጋ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

፻፲፰ኛው የእስክንድርያ ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ዳግማዊ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባደረጉላቸው ወዳጃዊ ጥሪ መሠረት ባለፈው ፳፻፯ ዓ.ም.፣ ከጥር ፩ – ፯ ቀን ድረስ በግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የስድስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ …

CNN በቅርቡ በጥናታዊ ምርምር የተገኙ ቦርጭን ለማጥፋት የሚጠቅሙ የምግብ አይነቶችን ዘርዝሯል። ስለዚህም እነዚህ የምግብ አይነቶች ጠቃሚ በመሆናቸው ላካፍላችሁ ወደድኩኝ። 1. ጭማቂዎች ከተለያዩ ፍራፍሬዎች የሚሰሩ ጭማቂዎች ለጤና ጠቃሚ የሆነ የቅባት አይነት ስላላቸው ከመጠን ያለፈ ቦርጭን ይከላከላሉ። ጭማቂዎቹን ሲያዘጋጁ ስኳር ባይጨምሩ ይመከራል። …

ቦርጭን ለማጥፋት የሚጠቅሙ የምግብ አይነቶች – ጥናታዊ ግኝት Read more »

ኢሳት ዜና (መስከረም 14 ፣ 2008) በማላዊ እስር ቤቶችን የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ 36 ህጻናትን ጨምሮ 387 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደሃገራቸው ለመመለስ ከአሜሪካ መንግስት በኩል ድጋፍ መገኘቱን የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት (IOM) ዛሬ አርብ ገለጠ። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ወደ ማላዊ በህገወጥ መንገድ ገብታችኋል ተብለው የተላለፈባቸውን የዘጠኝ ወራት የእስር ቅጣት ቢያጠናቅቁም ወደኢትዮጵያ የሚመልሳቸው አካል በመጥፋቱ በእስር …

ኢሳት ዜና (መስከረም 14 ፣ 2008) የግብፅ መንግስት በመገንባት ላይ ያለውን የአባይ ግድብን በልዩ የሳታላይት ቴክኖሎጂ እየተከታተለ እንደሆነ ዛሬ አርብ ይፋ አደረገ። ሰሞኑን በግብፅ መገናኛ ብዙሃን በግድቡ የውሃ መሙላት ሂደት በግብፅ ላይ የውኋ እጥረት ተፈጥሯል ሲሉ ላቀረቡት ዘገባ ምላሽን የሰጡት የሃገሪቱ ባለስልጣናት፣ በሳተላይት ቴክኖሎጂ በደተረገ ክትትል ግድቡን በውሃ የመሙላት ስራ እንዳልተጀመረ ሊረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል። በግብፅ …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከድርጅቱ በተገኘው መረጃ መሰረት በቀን ውስጥ ወደ ንቅናቄው ከሚደውሉ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ስልኮች መካከል 80 በመቶው ፣ ንቅናቄውን ለመቀላቀል መረጃ የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው። በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣው ደግሞ የማበረታቻ ሃሳቦችን ለመስጠት የሚፈልጉ ሰዎች ሲሆኑ፣ 2 በመቶ የሚሆነው ደግሞ መረጃ ለመስጠት የሚፈልገው ነው። የድርጅቱ የስልክ መረጃ አያያዝ እንደሚያመለክተው ካለፈው …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኤምባሲው የ2015 የዲቪ ሎተሪ የመጨረሻ ቀን ረቡዕ መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ.ም. መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን የቴክኒክና ሙያ የትምህርት ማስረጃን እንደሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ማስረጃነት ከዚህ ቀደም ሲቀበል መቆየቱን በማስታወስ ከአሁን በኃላ የማይቀበል መሆኑን አስታውቆአል፡፡ ኤምባሲው ይህን ለምን እንዳደረገ በመግለጫው የጠቀሰው ነገር ባይኖርም የኤምባሲው ምንጮች እንደጠቆሙት የአሜሪካ መንግስት …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በሀዲያ ዞን “አባ ሰንጋ” የተሰኘው የከብቶች በሽታ ተከስቶ በርካታ ሰዎችና ከብቶች ለሞት እየተዳረጉ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን እንዳጠናቀረው መረጃ እስካሁን በበሽታው አስራ ስድስት ሰዎች ሞተዋል። በበሽታው እጅግ በርካታ ከብቶች እያለቁ በመኾናቸውም የ አካባቢው ህዝብ መጪውን የመስቀል በዓል ከስጋ ተዋጽኦ ውጪ …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ከተማ በየካቲት ወር 2008 ጀምሮ ይከናወናል ተብሎ የታቀደው የፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታ ፕሮጀክት ከአዋጪነት አንጻር በሚገባ በጥናት ያልታየና በአሁኑ ሰዓት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን የሚያሳጣ ነው በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ነዋሪዎች እንደጠቆሙት ፕሮጀክቱ ከዊንጌት፣ በጎፋ ገብርኤል አድርጎ ወደ ጀሞ የሚዘልቅ ለከተማ አውቶቡስ ብቻ …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ ኢዞሎ ግዛት ውስጥ ድንበር አቋርጠው ለመሻገር ሲሞክሩ የተያዙት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በተጨናነቀ እስር ቤት ውስጥ በስቃይ ላይ እንደሚገኙ ኦል አፍሪካን ዘግቧል። በኬንያ ኢዞሎ ጂኬ እስር ቤት ውስጥ ከሚገኙት 450 እስረኞች መካከል 300 ዎቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። እስር ቤቱ ከ 150 የበለጡ እስረኞችን መያዝ እንደማይችል የኢዞሎ ግዛት ምክትል …

በአውሮፓ የተሻለ ህይወት ለመምራት ያሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች በሜዲትራንያን ባህር ሰምጠው ሞተዋል። ከነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ ወጣቶች ናቸው። የስደተኞቹ ጩኸት እና የድረሱልን ጥሪያቸው በሀገሮቻቸው ሰሚ አላገኘም።

የዲላ ዩኒቨርስቲ ሰራተኞች በፕሬዝዳንታቸው “ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ኮሬ” ላይ ዓመፅ በማስነሳት ወደ ትምህርት ምኒስቴር ጥያቄያቸው ልከዋል። ፕሬዝዳንቱ “ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ኮሬ” ላይ 16 ክሶች ቀርቦላቸዋል። ከክሰቹ መሃል ፩) ከ229 በላይ ሰራተኞች ከህግና ድንብ ውጪ በራሳቸው ስልጣን እንዲቀጠሩ ኣድርገዋል፣ ፪)ሰራተኞች ዩኒቨርስቲው …

የዲላ ዩኒቨርስቲ ሰራተኞች በዩንቨርስቲው ፕሬዚዳንት ላይ ኣመፅ ኣስነሱ። ዝርዝር ደብዳቤውን ይዘናል:: Read more »

ኢሳት ዜና (መስከረም 13, 2008) በኢትዮጵያ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ለምግብ እርዳታ የሚጋለጡ ሰዎች ቁጥርና የእርዳታ መጠን በቀጣዮቹ አራት ወራቶች በከፍተኛ መጠን ሊጨምር እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጀት አስታወቀ። የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር 4.5 ሚሊዮን አካባቢ እንደነበር ያወሳው ድርጀቱ፣ የተረጂዎችን ቁጥር ከታህሳስ ወር መጨረሻ ጀመሮ ጭማሪን እንደሚያሳይ ገልጿል። በፈረንጆቹ አዲስ አመት ባሉ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራቶች …

አስፋ ጫቦ Corpus Christi, Texas USA መስከረም ሲጠባ ፤አደይ ሲፈንዳ፤ እንኳን ሰው ዘመዱን ፤ ይፈልጋል ባዳ ማለት እውነት ነው!ለኔ፣የኔ እወነት ነው! ዳዊት “..ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ …፤ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ምድርም ሐሴት ታደርግ“  ያለው መሆኑ ነው።ዘፈን ዘፈን !ዝፈን ዝፈን! ብሎኛል እንደማለት ።ዳዊት የተናገረው በምናቡ ኢትዮጵያን እያየ መሆን አለበት። እንጅማ የሱ አገር በአበባ ሠምሮ፥ደምቆ፥ ሰውም፤ምድሪቱም የሚዘፍኑበት አይመስለኝም:: የሰሐራ በረሀ […]

The post ዮ ..ሀ.. ማስቃላ!! ….አደይ ሲፈንዳ!! (አስፋ ጫቦ ) appeared first on ሳተናው (Satenaw)-Latest Ethiopian News & Breaking News.

ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ በምትገኘው በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ የመጣው ቤተክርስቲያኒቷን ከህጋዊው ቦርድ አስተዳደር ነጥቆ ለወያኔው ሹመኛ ለአባ መላኩ (አቡነ ፋኑዔል) የማስረከብ ትንንቅ በዛሬው ዕለት ከፍ ወደአለ ደረጃ መሸጋገሩ ከስፍራው የደረሰን ሪፖርት ያመለክታል። …

ዶ/ር አክሊሉ ሐብቴ መፈንቅለ ቦርድ አወጁ Read more »

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየአመቱ በድምቀት የሚከበረው የኢድ አል አድሃ በአል ለ1 ሺ 436ኛ ጊዜ በኢትዮጵያና በመላው አለም ተከብሯል። በሳውድ አረቢያ መካ በአሉን ለማክበር በስፍራው ከተገኙ ከ2 ሚሊዮን በላይ የሃይማኖቱ ተከታዮች መካከል ከ700 ያላነሱ ሰዎች ተረጋገጥተው ህይወታቸው አልፎአል። ከ900 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በሰንአ በአንድ መስኪድ ላይ …

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማዬት የተሳናቸው ተማሪዎች መስከረም 11 ቀን 2008 ዓም ፣ ከመብት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በማንሳታቸው በፖሊሶች ክፉና የተደበደቡ ሲሆን፣ የተማሪዎችን ተወካዮች ጨምሮ 17 ማዬት የተሳናቸው ተማሪዎች ተይዘው ታስረዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ተማሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ፣ ተማሪዎች የማደሪያ ክፍል በአንድ ግቢ ውስጥ ለሚገኘው ኮሌጅ በመሰጠቱ ፣ ተማሪዎች እንዲመለስላቸው …

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ኢህአዴግ በመቀሌ ላይ ባደረገው ጉባኤ ግንባሩን ጥለው የሚወጡ ሰዎች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ መጨመሩን የገለጸ ቢሆንም፣ አሁንም ድርጅቱን ጥለው የሚወጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ፣ ግንባሩ የመልቀቂያ ጥያቄን እንደማያስተናግድ አስታውቋል። ድርጅቱን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡ አባላት አርፈው እንዲቀመጡ ተነግሯቸዋል። ለኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የመልቀቂያ ጥያቄ የሚያቀርቡ …

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዶ/ር ሽመልስ ከሌሎች ታዋቂ ምሁራንና ፖለቲከኞች ጋር በመሆን ቀስተደመናን ፓርቲ፣ ከዚያም ቅንጅት እንዲመሰረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። የቅንጅት መሪዎች በታሰሩበት ወቅትም ዶ/ር ሽመልስ፣ ትግሉ እንዳይቀዛቀዝ ከፍተኛ ስራ ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፣ አንድነት ፓርቲ በተመሰረተበት ወቅትም ፓርቲውን በአመራር አባልነት አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር የተቋቋመውና …

የቀድሞው የቅንጅት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የነበሩት እና የታዋቂው የታሪክ ተመራማሪ እና ጸሃፊ የአቶ ተክለጻዲቅ መኩሪያ ልጅ የሆኑት ዶክተር ሽመልስ ተክለጻዲቅ መኩሪያ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል::ዶክተር ሽመልስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት እና መብት በመታገል ያበረከቱት አስታውጾ ታሪክ አይረሳውም::በዶክተር ሽመልስ ሞት የተሰማኝን ጥልቅ …

ዶክተር ሽመልስ ተክለጻዲቅ መኩሪያ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ:: Read more »

  በዛሬው እለት በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞን(በመላው ኢትዮጵያ) የኢድ አል አድሃ በአል በደመቀ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ በተለመደው መልኩ በሰላም በፍቅር እና በትእግስት የስላቱን ፕሮግራም አጠናቆ ወደ ቤቱ ሲመለስ በአንዳንድ አከባቢዎች ፖሊሶች ለመተናኮል ቢያስቡም እጅግ የሰላም እና …

የ1436ኛው የኢድ አድሃ በአል በኢትዮጵያ በድምቀት የተከበረ ሲሆን ፖሊሶች ለመተናኮስ ሲሞክሩ ታይተዋል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ 4ሺ በላይ የመንግስት ሰራተኞች ላይ እርምጃ የወሰደው የከተማዋ አስተዳደር በአስር ክፍለ ከተሞች ሹምሽር አካሄዷል። ከቀናት በፊት በተጀመረው በዚሁ ሹም ሽር በ116 ወረዳዎች የሚገኙ ከ100 በላይ አመራሮች የተነሱ ሲሆን የከተማዋ አስተዳደር ድርጊቱ ከትምህርት ብቃት ጋር የተገናኘ እንደሆነ መግለፁን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። …

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) ኢትዮጵያን ጨምሮ በድሃ ሃገራት ከሚኖሩ ህዝቦች መካከል 90% የሚሆኑት የኢንተርኔት ተጠቃሚ አለመሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። ከአፍሪካ ዝቅተኛ የኢንተርኔት ሽፋን ያላት ኢትዮጵያም በአለም በአገልግሎቱ አሳሳቢ ተብለው ከተፈረጁ አስር አገራት መካከል አንዷ መሆኗን ድርጅቱ በአመታዊ ረፖርቱ ገልጿል። ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ቡሩንዲ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ረፐብሊክ፣ ጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክና፣ …

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) ከኢትዮጵያ የሚደረገውን ከፍተኛ የወጣቶች ስደት ተከትሎ የአውሮፓ ህበረት ልዩ የሉዑካን ቡድን በጉዳዩ ዙሪያ ለመምከር ወደአዲስ አበባ መጓዙን ህብረቱ ዛሬ ረቡዕ ገለጠ። በሃገሪቱ የሶስት ቀን ቆይታ የሚኖረው ይኸው የልዑካን ቡድን ከኢትዮጵያ እየጨመረ በመጣው የወጣቶች ስደት እና ችግሩ በሚቀንስበት ዙሪያ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ሰፊ ምክክር ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል። የአለም አቀፉ የስደተኞች …

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አምስት ከፍተኛ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አመራሮችን ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተገናኘ ዛሬ ረቡዕ ከሃላፊነታቸው አነሳ። የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታና የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር ዶ/ር አበራ ደሬሳ፣ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ፣ እንዲሁም ሁለት ምክትል ፕሬዚዳንቶች አቶ ቶሎሳ በየነና፣ አቶ አበበ ጥላሁን ከባንኩ አመራርነት መነሳታቸው ታውቋል። የኦሮሚያ ህብረት …

የዒድ አል አድሐ በዓልን አስመልክቶ በእስር ከሚገኙ መሪዎቻችን የተሰጠ መግለጫ ረቡእ መስከረም 12/2008 የመግለጫው ፒዲኤፍ ቅጂ ሊንክ፡- http://goo.gl/XfMlRP የመግለጫው ሙሉ ቃል በጽሁፍ፡- ******************************* ******************************* በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ፣ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው! ጥያቄዎቻችን እስኪመለሱ እና ብሄራዊ የሃይማኖት ጭቆናው እስከሚያከትም …

የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሆይ! – የዒድ አል አድሐ በዓልን አስመልክቶ በእስር ከሚገኙ መሪዎቻችን የተሰጠ መግለጫ Read more »

‎- የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለእደለኞቹ አይታደሉም ተባለ ‎- በዘንድሮ የትምህርት ዘመን የመጽሐፍት እጥረት መኖሩ ታወቀ – የቡርኪና ፋሲ የመከላከያ ሰራዊት መፈንቅለ መንግስት ላካሄዱት ክፍሎች የጊዜ ገደብ ያለው ማስጠንቀቂያ ሰጠ. ‎- የግብጽ መንግስት በግብጽና በጋዛ ወሰን የሚገኙ ከሶስት ሺ በላይ ቤቶችን አፍረሰ፣ …

– የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለእደለኞቹ አይታደሉም ተባለ ‎- በዘንድሮ የትምህርት ዘመን የመጽሐፍት እጥረት መኖሩ ታወቀ:: Read more »

በመጪው እሁድ መስከረም 16 ቀን 2008 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ህዝቡ በመንግስት ላይ ጠንከር ያለ ተቃወሞ ሊያስተጋባ እና ለያሰማ ይችላል በሚል ስጋት ውስጥ የወደቀው የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት የፀጥታ ሀይሎች የሚላቸው አካላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ መመሪያ መተላለፉን ውስጥ …

በደመራ በአል ወቅት ረብሻ ሊነሳ ይችላል በሚል ስጋት የፀጥታ ሀይሎች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ መመሪያ ተላለፈ:: Read more »

Minilik Salsawi – አምባገነን መንግስታት ወንጀላቸው እየበዛ መውጪያ ቀዳዳ እያጡ ሲሄዱ በሕዝብ ጫንቃ ላይ ተቀምጠው የሕዝብ ጥያቄ መመለስ ሲያቅታቸው በከፍተኛ ደረጃ ዘረፋ ውስጥ ሲዘፈቁ ሕዝብን በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ለመሸንገል የሚያደርጉት መፍጨርጨር ሕዝቡ ከነሱ ቀድሞ እንደሚያውቅ ይዘነጋሉ አሊያም እንደለመዱት በሃይል ለመቀጠል ደፋ …

በፕሮፓጋንዳ ቀውስ የሚዋዥቀው የወያኔው ጉጅሌ አገዛዝ (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

ቪዛ ሳትጠይቅ፣ ከሰው ብላ ጠጋ እጂጉን ተጣጥፋ በላስቲክ ታሽጋ ባህሩን አቋርጣ እሷ እኛን ፍለጋ በዶላር ከፍ ብላ ልታወጣ ዋጋ እሷም እነጄራይቱ መጥታለች እኛው ጋ የሀገሬ ዜጎች ድሆቹ ሳይጠግቡ ከአፋቸው ላይ ነጥቀው እኛን ሊመግቡ ሀብታሞች ጨክነው የእንጄራ ነግድ ገቡ። እርም ነው …

እንጄራም ተሰዳ! ልያ ፋነታ ከዋሽንግተን ዲሲ Read more »

በዚህ ቭድዮ በአይሲስ የተጠቁ ግፍ የተፈጸመባቸው ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ::የሰሃራን በረሃ አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለተሻለ ኑሮ ሲሄዱ በዚህ 2015 ከ2000በላይ ስደተኞች ሞተዋል:: [youtube http://www.youtube.com/watch?v=QsdYXjzB9Yw]   https://news.vice.com/video/witness-to-islamic-state-atrocities-extra-scene-from-libyas-migrant-trade

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፣ በተለምዶ ውቤ በረሃ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን (አራዳ ጊዮርጊስ) አዲሱ የባቡር ተርሚናል እስከ አፍንጮ በር የሚገኙ ነጋዴዎች፣ ምትክ

የንግድ ቦታ ሳይሰጣቸው የንግድ ቤቶቻቸውን በግዳጅ ለማፍረስ ወረው እያሸገ መሆኑን ገለጹ፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር እኩል ሊባል የሚችል ዕድሜ ያስቆጠሩ ንግድ ቤቶች በአንድ ሳምንት ማስጠንቀቂያ ማፍረስ ተገቢ አለመሆኑን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ፣ አስተዳደሩ የገባላቸውን ቃል በማጠፍ፣ ‹‹ተለዋጭ ቦታ የምሰጣችሁ አሁን ያላችሁበትን የንግድ ቦታ አፅድቼ ስጨርስ ነው›› ማለቱ፣ ከሕግም ሆነ ከመንግሥት ፖሊሲ አንፃር የዜጐችን መብት የማያስከብር በመሆኑ አግባብነት የለውም ብለዋል፡፡ 

የከተማ አስተዳደሩ ነጋዴዎቹን ከዓመት በፊት ሰብስቦ በአክሲዮን እንዲደራጁና እያንዳንዳቸው 25,000 ብር በማዋጣት በባንክ እንዲያስቀምጡ፣ እንዲሁም በየወሩ ከ2000 ብር በላይ ገቢ እንዲያደርጉ ያቀረበውን ሐሳብ መቀበላቸውንና ተግባራዊ ማድረጋቸውን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ፣ በንግድ ቦታቸው ላይ ግንባታ ተካሂዶ እያንዳንዳቸው 25 ካሬ ሜትር ቦታ እንደሚሰጣቸው የተነገራቸው ሁሉ ታጥፎ፣ በቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ መወሰኑ እንዳስደነገጣቸው ተናግረዋል፡፡ 

መንግሥት ከወሰነ በኋላ የገባውን ቃል ተላልፎ በአስቸኳይ እንዲለቁ የሚያደርግ ከሆነ፣ ለሌሎች የልማት ተነሺ ነጋዴዎች የተሰጠው ዕድል ለእነሱም መነፈግ ስለሌለበት፣ ተለዋጭ የኮንዶሚኒየም የንግድ ቦታዎች እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ቤተሰቦቻቸውንና ቀደምት ነጋዴዎችን በመተካት ሥራቸውን በንግድ ላይ በማድረግ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት፣ የሚመግቡትና ራሳቸውንም እያኖሩ የሚገኙት በያዙት ንግድ ቤት እየነገዱ በሚያገኙት ገቢ መሆኑን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ፣ በሕገወጥ መንገድ በ‹‹አፍራሽ ግብረ ኃይል›› አማካይነት ወደ ጎዳና ተገፍተው ከመጣላቸው በፊት መንግሥት ሊደርስላቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ 

ዕድሜ ጠገብ የንግድ ቤቶች ከሆኑት መካከል የታዋቂው ክራር ተጫዋች ከተማ መኰንን ቤት የነበረው አሁን ብሔራዊ ሆቴል በቅጽል ስሟ ‹‹ጭራ ቀረሽ›› በሚል መጠሪያ የምትታወቀው የዘነበች ታደሰ የነበረውና አሁን ግሪን ባርና ሬስቶራንት፣ መዲና በመባል የሚታወቀው አሁን ያሲን ሱፐር ማርኬት፣ ድምፃዊት አበበች ደራራ የነበረችበት አሁን ሰላም ልኳንዳ፣ ዘመናት ያስቆጠረው አባ ገዳ ማተሚያ ቤት፣ አርቲስት አሰለፈች አላምረው ትሠራበት የነበረው ሆቴል፣ ኤፍሬም ግሮሰሪና ሌሎችም ታዋቂ የንግድ ቤቶች የሚፈርሱ መሆናቸውንም ነጋዴዎቹ ገልጸዋል፡፡

መንግሥት ለልማት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን እነሱም የሚደግፉት ተግባር እንደሆነ የገለጹት ነጋዴዎቹ፣ ከሁሉም በፊት የዜጐች መብትና ክብር መቅደም ስላለበት፣ እንዲሁም መንግሥት ዜጐቹን የመንከባከብና እንደየሥራ ዘርፋቸው ማሰማራት የሚጠበቅበት በመሆኑ ምትክ ቦታ ሰጥቶ እንዲታደጋቸው ጠይቀዋል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ የቀድሞ ቀበሌ 03/09 (ወረዳ 5) አስተዳደር፣ በደል ሊፈጽምባቸው መሆኑን እየገለጹ ስለሚገኙት የውቤ በረሃ ነጋዴዎች ጉዳይ ለማነጋገር ሪፖርተር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

በተመሳሳይ ከአራዳ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደርና ከተማ ማደስ ጽሕፈት ቤቶችም በተመሳሳይ ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡   

 

የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት አብዛኛዎቹን የክፍላተ ከተሞችና የወረዳ አመራሮች በማንሳት፣ በአዳዲስ አመራሮች እየተካ መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት

ወረዳዎችና ክፍላተ ከተሞች መመራት ያለባቸው ዲፕሎማና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ባላቸው መሆን አለበት የሚል አዲስ አቋም መያዙ፣ ለሹም ሽሩ ምክንያት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሠረት በአሥሩም ክፍላተ ከተሞችና በሥራቸው በሚገኙ 116 ወረዳዎች የሚገኙ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አመራሮች ተነስተዋል፡፡ በተጨማሪም ሹም ሽሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰፈነውን የመልካም አስተዳደርና የሙሰኝነት ችግር ለመቅረፍ መንግሥት ከያዘው ዕቅድ ጋር የሚያያዝ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ይህን ችግር ለመቅረፍ በቅድሚያ ይህ ችግር ያለባቸው አመራሮች ተገምግመው እንዲነሱ መደረጉም ተገልጿል፡፡ ለማሳያ ያህል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ 12 ወረዳዎች ከዲፕሎማ በታች ያላቸው አመራሮች 70 የሚጠጉ ሲሆን፣ እነዚህ ሁሉ እንደተነሱ ተገልጿል፡፡ በሙስናና በተለያዩ ግድፈቶች ደግሞ 30 አመራሮች እንዲነሱ መደረጉም ተመልክቷል፡፡ 

በሌሎች ክፍላተ ከተሞችና በሥራቸው በሚገኙ ቀበሌዎችም በተመሳሳይ ከ100 ያላነሱ አመራሮች በእነዚህ ሁለት ምክንያቶች መነሳታቸው ተገልጿል፡፡ ይሁንና ከዲፕሎማ በታች የትምህርት ደረጃ ኖሯቸው አመራር ሲሰጡ የቆዩ አባላት ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት እነዚህ አመራሮች ትምህርት ለመማር ጥያቄ  በሚያቀርቡበት ወቅት መንግሥት ቅድሚያ ሥራችሁን ሥሩ የሚል ምላሽ የሰጣቸው በመሆኑ ትምህርት መማር እንዳልቻሉ አስታውሰው፣ ውሳኔው ፍትሐዊ እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡ 

በአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ይህንን አለመግባባት ለማስቀረት የውይይት መድረኮች ፈጥሮ እንደነበርም ታውቋል፡፡ በዚህም ያላቸው የትምህርት ደረጃ ዝቅተኛ በመሆኑ የተነሱ አመራሮች የሦስት ወራት ደመወዝ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ሥራዎችን እንዲሠሩ ወይም ዕድሜያቸው ለጡረታ የደረሰው ደግሞ በጡረታ እንዲገለሉ ሐሳብ ቀርቦ፣ ከሞላ ጎደል መግባባት ላይ መደረሱ ተመልክቷል፡፡

ዋነኛው የአዲስ አበባ ከተማ ችግር የመልካም አስተዳደር እጦትና ኪራይ ሰብሳቢነት [ሙስና] እንደሆነ ነዋሪዎች ባገኙት አጋጣሚ ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ ይህ ችግር የ2007 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም በሚገመገምበት ወቅት በሰፊው ተነስቷል፡፡ በተለይ በመሬት፣ በንግድና በአገልግሎት መስጫ ዘርፎች ላይ ኅብረተሰቡ ከፍተኛ እሮሮ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

በእነዚህ ዘርፎች ለተገልጋዮች ተገቢውን አገልግሎት አለመስጠት፣ ተገልጋዮችን ለማስተናገድ ዝግጁ አለመሆን፣ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ውሳኔ አለመስጠት፣ ‹‹ጉዳዩ አልታየም›› በማለት ተገልጋዮችን ማጉላላትና ጉቦ መጠየቅ ከሚቀርቡት ቅሬታዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በንግድ በኩል የንግድ ፈቃድ ዕድሳት፣ የንግድ ስያሜ አሰጣጥ፣ የንግድ አድራሻ ማረጋገጫ አሰጣጥ፣ ሕገወጥ ንግድ በሰፊው የሚታዩ ችግሮች ከመሆናቸውም በተጨማሪ፣ በአጠቃላይ የንግድ ሥርዓቱ የተተረማመሰ እንደሆነ ቅሬታ ይቀርባል፡፡

በእነዚህ ሁሉ ችግሮች ሙስና ዋነኛ መገለጫ መሆኑ ከኅብረተሰቡ በሰፊው የሚነሳ ጉዳይ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህንን የኅብረተሰብ ሮሮ በመቀበል፣ የራሱን ግምገማ አካሂዶ ችግሩ እንዳለ አምኗል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ ከሕዝብ ጋር ተወያይቶ ወደ ተግባር እንደሚገባ ገልጾ ነበር፡፡ 

ይህንን ችግር ለመፍታት በተካሄዱ ተከታታይ ግምገማዎች ግድፈት እንዳለባቸው የተለዩ አመራሮችን ከክፍላተ ከተሞችም ሆነ ከወረዳዎች ማንሳት ዋነኛ ዕርምጃ ሆኗል፡፡

በዚህ መሠረት ቢያንስ ችግሩ ጎልቶ በሚታይባቸው ክፍላተ ከተሞች ከ30 በላይ አመራሮች፣ በወረዳ ደረጃም በተመሳሳይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አመራሮች እንደተነሱ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ 

ይሁንና በአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ባለቤትነት የሚካሄደው ይህ ሹም ሽር ባለፈው ሳምንት መገባደዱን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃን ሥራው እየተካሄደ መሆኑን ለሪፖርተር አረጋግጠው፣ ሥራው ባለመጠናቀቁ መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡ 

ከዚህ በመቀጠል የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በማዕከል ደረጃ የሚገኙ ቢሮዎችንና ኤጀንሲዎችን የሚመሩ አመራሮች ላይ ሹም ሽሩን እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡ ሹም ሽሩ በርካታ አመራሮችን ከካቢኔ የሚያስወጣና በምትካቸው አዳዲስ የካቢኔ አባላትን እንደሚሾም ምንጮች ተናግረዋል፡፡

የካቢኔ አባላቱ ሹም ሽር በቅርቡ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

 

በ1920ዎቹ ማብቂያ ኢትዮጵያን የወረረው የፋሽስት ኢጣሊያ ጦር በወቅቱ በዓለም ዙሪያ የተከለከሉ የጦር መሳሪይዎችን በመጠቀም ሰላማዊ ሰዎችን ጭምር ሳይቀር መግደሉን ያትታሉ አቶ ኪዳኔ፤ የፋሽስት ጦር ከቫቲካን ድጋፍ እንደነበረው ይናገራሉ።

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሆላንዱ ዴልታሬስ ኩባንያ ከፈረንሳዩ ቢአር ኤል አይ ኩባንያ ጋር በመሆን በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ጥናት እንዲያካሂድ በግብጽና በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተወክሎ ነበር። ይሁን እንጅ ጥናቱ ከመጀመሩ በፊት በምን መንገድ መካሄድ አለበት በሚለው ነጥብ ዙሪያ ከፈረንሳዩ ኩባንያ ጋር ሲነጋገሩ ቢቆዩም መስማማት አልቻሉም። ኩባንያው ከኢሳት ለቀረበለት የጽሁፍ ጥያቄ …

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኮምሽነሩ ሰሞኑን በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለጉዳዩ በሰጡት ማብራሪያ ከ95 ሺህ በላይ ተሿሚ፣ ተመራጮችና የመንግስት ሠራተኞች ሐብት ኮምሽኑ መመዝገቡን፣ እንዲሁም ከ14 ሺህ በላይ ሐብት አስመዝጋቢዎች የቤተሰቦቻቸውን ሐብት አሳውቀው ማስመዝገባቸውን አረጋግጠዋል፡፡ «ይህ መረጃ ለምን ይፋ አይደረግም» ለሚለው ጥያቄም ሲመልሱ ለመገናኛ ብዙሃን የመናገር ግዴታ እንደሌለባቸው በመግለጽ …

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ ውቤ በረሃ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እስከ አፍንጮ በር የሚገኙ ነጋዴዎች፣ ምትክ የንግድ ቦታ ሳይሰጣቸው የንግድ ቤቶቻቸውን በግዳጅ ለማፍረስ እየታሸጉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ። የከተማው አስተዳደር ነጋዴዎቹን ከዓመት በፊት ሰብስቦ በአክሲዮን እንዲደራጁና …

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው አገሪቱ የሚታየው የስኳር እጥረት እልባት ባያገኝም፣ በደቡብ ክልል እጥረቱ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ህዝቡ ለሻሂ የሚሆን ስኳር ማግኘት አለመቻሉን እየተናገሩ ነው። በሌላ በኩል ግን በኢህአዴግ የአንድ ለአምስት የጥርነፋ ስልት የቡድን መሪ የሆኑ ነጋዴዎች፣ መንግስት የሚያከፋፍለውን ስኳር፣ እየጫኑ ወደ አልታወቀ ቦታ …

ከቅርብ አመታት ወዲህ በሀገሪቱ ውስጥ እየታየ ያለው የቋንቋ ግድፈትና የቋንቋ አጠቃቀም ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ህጻናትን “አማርኛ መናገርና ድንጋይ መወርወር ሁለቱም ወንጀል ናቸው።” ብሎ እስከ ማስተማር የደረሱ ትምህርት ቤቶችን አፈራን። ስህተት ነው ይታረም ስንል ተንጫጫን~ ችግሩ ግን ዛሬም ድረስ …

ከስህተት ወደ ጥፋት የተሸጋገረው የቋንቋ ግድፈታችን! (የትነበርክ ታደለ) Read more »

በአንድ ወገን — ብቸኛ የኢትዮጵያ ባለቤቶችና ጠበቆች — በሌላ በኩል ኢትዮጵያዊነት የማይዋጥላቸው// ሁለቱም በትናንት ላይ ተቸክለው በአንድ በኩል ራሳቸውን የኢትዮጵያ መስራች፣ በሌላ በኩል ራሳቸውን በግዳጅ ኢትዮጵያዊ የተደረጉ አርገው የሚያስቡ ዛሬን መኖር፣ ነገን መመልከት ያልቻሉ፤ ሁለቱም ወገኖች ከዓለም የአገር አመሰራረት ታሪክ …

ሁለቱ ጽንፎች ሲጓተቱ– አልነጋ አለ ሌ’ቱ// – ግርማ በቀለ Read more »