ሶስቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች የአዳጊ ክልሎችን ሪፖርት አዳማጡ
መጋቢት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ልዩ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል በሚል ክልሎችን ህወሃት፣ ብአዴንና ኦህዴድ እንዲያስተዳድሩዋቸው ካከፋፈለ በሁዋላ፣ የክልሎችን የመጀመሪያ ሪፖርት ሰሞኑን ተቀብሎአል፡ ኢሳት ቀደም ብሎ በሰራው ዘገባ የሶማሊ ክልል በህወሃት፣ ሃረሪ በኦህዴድና ህወሃት፣ አፋር በህወሃት፣ ቤንሻንጉል በብአዴን እንዲሁም ጋምቤላ በህወሃት እንዲተዳደሩ መወሰኑን ዘግቦ ነበር። እነዚህ አዳጊ የተባሉ ክልሎች ማንኛውንም የስራ እንቅስቃሴያቸውንና እቅዶቻቸውን ለእነዚህ …