ተመላሽ ወታደሮች ስርአቱን እንዲታደጉ የብአዴን አመራሮች ተማጽኖ አቀረቡ
መጋቢት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለስልጣኖቹ በባህርዳር ከተማ በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ የተመላሽ ሰራዊት አባላትን ሰብስበው ስርአቱ አደጋ ውስጥ በመግባቱ እንዲታደጉት ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ከምርጫው ጋር ተያይዞ ልማቱን ለማስቀጠል አደጋ ውስጥ ገብተናል ያሉት ባለስልጣናቱ፣ የተቀናሽ ሰራዊት አባላት በምርጫው ንቁ ተሳተፎ በማድረግ ስርአቱን እንዲታደጉ ተማጽነዋል። የሰራዊቱ አባላት “የቦታ ባለቤት እናደርጋችሁዋለን” ተብሎ ቃል የተገባላቸው ሲሆን፣ የፊታችን ቅዳሜ …