የጌዲዮ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች በረሀብ መጠቃታቸውን የሚያመለክት ደብዳቤ ተፈራርመው ለዞኑ መስተዳድር አቀረቡ
ታህሳስ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጌዲዮ ዞን በሚገኙ 9 ወረዳዎች ውስጥ በዚህ ወር ውስጥ ባልተለመደ ሁኔታ ከፍተኛ ረሀብ በመከሰቱ የዞኑ የአገር ሽማግሌዎች ህዝቡ ያለበትን አሳሳቢ ሁኔታ በመግለጽ የተፈራረሙበትን ደብዳቤ ዛሬ ለዞኑ መስተዳድር አስገብተዋል። በከፍተኛ ደረጃ ተደናገጡት የዞኑ ባለስልጣናት መረጃው ይፋ እንዳይወጣ ለማድረግ ዛሬ ቀኑን ሙሉ በስብሰባ ተወጥረው መዋላቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የአገር ሽማግሌዎቹ የገጠሩ …