ህዳር ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ተባብሶ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ የሳውዲን መንግስት ለመቃወም በሳውድ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ተቃውሞዋቸውን ለመግለጽ የወጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በፌደራል ፖሊሶች ተደብድበዋል። ከ100 በላይ ሰዎች ታስረው የነበረ ሲሆን እስከ ምሽት ድረስ 40 የሚሆኑት ተለቀዋል። ሰልፉን ያዘጋጀው የሰማያዊ ፓርቲ 15 የአመራር አካላትም በእስር ላይ …

ህዳር ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአውሮፓና አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮያውያን በሰልፍ ተቃውሟቸውን ሲገልፁ ውለዋል። በሳዑዲ ዐረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍ ተባብሶ መቀጠሉን ተጠቂዎቹ ለኢሳት ገለፁ። በሪያድ  ወደማጎሪያ ካምፕ ውስጥ  የተወሰዱ ኢትዮጵያውያን ካሉበት ስፍራ ሆነው ለ ኢሳት በስልክ እንደገለፁት፤ በትናንትናው ዕለት ብቻ  በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በከባድ መኪናዎች እየተጫኑ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። ስደተኞቹ-ለሳዑዲ ፖሊሶች፦” ወደ …

ህዳር ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህዳር እና የታህሳስ ወራትን  በሙሉ በጾም በጾሎት ምእመኑ እግዚኦታ እንዲያሰማ ቄስ አለሙ ሺጣ የኢትዩጵያውያን ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ዋና ጽሓፊ በአምላክ ስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በኢትዩጵያ በአሁኑ ስዓት እየተሰተዋለ ላለው ችግር ፣በምስራቅ አፍሪካ እና በአፍሪካ ሐገራት እንዲሁም በአለም ለሚታየውና ለሚሰማው በደል- ሀይማኖቱ በሚጠይቀው ስርዓት እጆችን ወደ አምለክ እንድናነሳ እና እንድናለቅስ …

ህዳር ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሸንጎው ከፍተኛ የአመራር ምክርቤትቅዳሜ ጥቅምት 29፣ 2006 ባደረገው ስብሰባ በሳዑዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በሀገሪቱመንግስት የጸጥታ ሀይሎችእየደረሰ ያለውን ህገወጥ እስራት፣ድብደባና ስቃይ በታላቅ ሀዘንና አንክሮ እንዳጤነው ገል ል። ሸንጎው  ለዚህ ግፍ ሰለባዎችና ለቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ሀዘን  በመግለጽ  ከጎናቸው እንደሚቆምምአረጋግጧል። በተመሣሳይ የ ኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ( ኢህአፓ) ሳውዲ አረብያ በዜጎቻችን ላይ …

ህዳር ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሴቶች ካምፕ ያለው ሁኔታ እጅግ አስከፊ መሆኑን ኢትዮጵያውያን ሴቶች ይነጋራሉ። ቀን በጸሀይ ማታ ደግሞ በብርድ እንድናሳልፍ እየተገደድን ነው የምትለው ሌላዋ እስረኛ ሳሚራ፣ ህጻናት እና እናቶች በምግብ እጦት እየተጎዱ ለበሽታም እየተዳረጉ ነው ትላለች። ባለፉት አራት ቀናት የወለዱ እናቶች መኖራቸውን የምትገልጸው ሳሚራ፣ የሳውዲ ፖሊሶች ወላዶችን የት እንደወሰዱዋቸው እንደማታውቅ ገልጻለች። ሀብታም የተባለቸውም …

ህዳር ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ ለኢሳት እንደገለጸው ምንም እንኳ የአዲስ አበባ መስተዳድር ፈቃድ ክፍል ፣ የሰላማዊ ሰልፍ መጠየቂያ ደብዳቤውን እንደማይቀበል ቢገልጽም፣ ፓርቲው ተቃውሞውን በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ለማድረግ ወስኖ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት ተባብሮ ተቃውሞ ማዘጋጀት ሲገባው፣ ፓርቲው እንዳያዘጋጅ መከልከሉ እንዳስገረመው ወጣት አሬድ …

ህዳር ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ፣ የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት ካንውነስል፣ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር በደቡብ አፍሪካ፣ ሂውማን ራይተስ ሊግ በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም መድረክ ድርጊቱን የሚያወግዙ መግለጫዎችን ለኢሳት ልከዋል።  

ህዳር ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት 5 ቀናት ጀምሮ በሳውዲ አረብያ በተለያዩ የማጎሪያ ጣቢያዎች ታስረው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እንደቀጠለ ሲሆን፣ በዛሬው እለት 2 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። ኢትዮጵያውያኑ እንደሚናገሩት ሰዎቹ የተገደሉት ባልና ሚስቶችን ለመለያየት በተደረገ ሙከራ ላይ በተፈጠረ ግርግር ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከሳዑዲው  አቻቸው ልዑል ሳውድ አል …

ህዳር ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አልሸባብ የተባለው አሸባሪ ቡድን እና በኤርትራ መንግስት እገዛ የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች በኢትዮጽያ ውስጥ የተለያዩ ስፍራዎች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጁ መሆናቸውን የሚያሳይ አስተማማኝ መረጃ ያለው መሆኑን የብሄራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል ጥቅምት 27 ቀን 2006 ዓ.ም ካስታወቁ በኃላ በአዲስአበባ በመንግስት በግል ተቋማት ከወትሮው የተለየ ፍተሻ …

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ሃለፊ በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብራዊ ደህንነት አማካሪ በአቶ ጸጋየ በርሄ ቁጥጥር የተመራና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎች ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ ከሸፈ። ከግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ለግድያ የተላከው ሙሉቀን መስፍን የተባለው ግለሰብ በትናንትናው እለት በቁጥጥር …

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክር ቤቱ ነገ በሚያደርገው ስብሰባ ለመንግስት ስልጣን አስጊ ሆኗል ባለው የሽብርተኝነት አደጋ ላይ እንደሚመክር ለማወቅ ተችሎአል። ምክር ቤቱ ከፍተኛ ስጋት ደቅነዋል ባላቸው ግንቦት7 እና የኤርትራ መንግስት ላይ ተነጋግሮ የመፍትሄ እርምጃ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። ምክር ቤቱ በሳውዲ አረቢያ በካምፕ ውስጥ ስላሉ ኢትዮጵያም ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ …

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮምሽን በመካሄድ ላይ ባለው 6ኛው የአፍሪካ ሚዲያ አመራሮች ፎረም ላይ ኢህአዴግ የሚያቀነቅነው  የልማታዊ ጋዜጠኝነት ጽንሰ-ሀሳብ በአፍሪካ ጋዜጠኞች ተተችቶአል። ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ችግሮቻቸውን ፊትለፊት አውጥተው መናገር ባለመቻላቸውም ወቀሳ ደርሶባቸዋል። ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በዚሁ ጉባዔ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የፕሬስ ነጻነት በኢትዮጽያ መረጋገጡን በማውሳት ፕሬሱ ግን በውስጡ …

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በሶማሊ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ የሚታየው ሁኔታ እስከ ዛሬ ከታዩት ሁሉ የተለየ ነው ይላሉ ነዋሪዎች። ከሌሎች አካባቢዎች በመሄድ ወደ ከተማው መግባት ወይም ከከተማው በመውጣት ወደ ሌሎች አካባቢዎች መሄድ  የተከለከለ ነው ይላሉ። የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከተማው በብዛት በመገኘት ቤት ለቤት የሚያካሂዱት ፍተሻ ለነዋሪዎች ጭንቀትን ፈጥሮባቸዋል። በክልሉ ፕሬዚዳንት ትእዛዝ …

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየካ ክፍለ ከተማ በቀድሞ አጠራሩ ከፍተኛ 12 ቀበሌ 18 ለህዝብ አገልግሎት በሚል የተሰራው ጤና ጣቢያ ካለፉት 6 ወራት ጀምሮ የእስረኞች ማጎሪያ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሆን መደረጉን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የአካባቢው ነዋሪ በቂ የህክምና ቦታ አጥቶ በሚቸገርበት ጊዜ ፣ መንግስት ጤና ጣቢያውን ፖሊስ ጣቢያ ማድረጉ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። በጉዳዩ …

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ የሚማሩ ተማሪዎች ከማንነት እና መብት መከበር ጋር በተያያዘ ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ የአንደኛ እና መለስተኛ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ትምህርት ማቆማቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ተማሪዎቹ በቋንቋችን እንማር፣ በአካባቢያችን የሚታየው የመብት ረገጣ ይቁም የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳታቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የፌደራል ፖሊስ አካባቢውን ከተቆጣጠረው በሁዋላ ቁጥራቸው ከ25 …

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመሬት፣  ከኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቱ ለቀረቡ 990 ሺ 627 አቤቱታዎች  መንግስት መልስ ለመስጠት እንደተሳነው መረጃዎች አመልክተዋል። የመልካም አስተዳደር ኮማንድ ፖስት ሴክሬታርያት ፅ/ቤት የ2005 የ6 ወራት የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚያሳየው ከመሬት፣  ከኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቱ ለቀረቡ 990 ሺ 627 አቤቱታዎች …

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ወሎ ዞን በእያንዳንዱ ቀበሌ  10 ሰዎች እየተመለመሉ አሸባሪዎችን ነቅተው እንዲጠብቁ ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑን አርሶ አደሮች ተናግረዋል። በስልጠናው የተነሳ አዝመራችንን እንኳ በወቅቱ ለመሰብሰብ አልቻልንም የሚሉት አርሶደአሮች፣ በአካባቢያቸው ጸረ ሰላም ሀይሎች ሲንቀሳቀሱ ከተመለከቱ ወይም ጸጉረ ልውጦችን ከተመለከቱ ለመንግስት አካላት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተነግሮአቸዋል። ለሁለት ሳምንት በሚቆየው በዚህ ስልጠና አርሶአደሮቹ …

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጉራጌ ዞን የእንድብር ከተማ  ነዋሪዎች እንደተናገሩት በከተማቸው ካለፉት 5 ቀናት ጀምሮ መብራት በመጥፋቱ እናቶች እህል አስፈጭተው ልጆቻቸውን መመገብ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። አቅሙ ያላቸው 30 ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው ወልቂጤ ከተማ በመሄድ እህል ለማስፈጨት መቻላቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ አቅሙ የሌላቸው ግለሰቦች ግን ይህን ማድረግ ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል ብለዋል። …

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የስዊዝ ሳይንቲስቶችን የምርመራ ውጤት በመጥቀስ አልጀዚራ  እንደዘገበው፤ በያሲር አራፋት ሰውነት ውስጥ ከመጠን ያለፈ ፖሎኒየም የተሰኘ የራዲዮ አክቲቭ ንጥረ ነገር ክምችት ተገኝቷል። ይሁንና እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2004 ለሞት የተዳረጉት ያሲር አራፋት በፖሎኒየም የተመረዙት መቼ እንደሆነ የሳይንቲስቶቹ ጥናት አያመለክትም። የምርመራ ጥናቱ ውጤት በያሲር አራፋት አስከሬን ውስጥ ከትክክለኛው መጠን   የ …

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጋር በተያያዘ አንዴ ሲሞቅ ሌላ ጊዜ ሲቀዘቅዝ የነበረው የቁጫ ተቃውሞ በዛሬው እለት በሰላም በር ከተማ ተጠናክሮ መካሄዱን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመልክታል። ዛሬ ተቃውሞውን ያካሄዱት ተማሪዎች ሲሆኑ ፣ ተማሪዎችም ላቀረብነው ጥያቄ መልስ የማይሰጠን ከሆነ ትምህርት አንማርም ብለዋል። ተቃውሞውን አስተባብረዋል የተባሉ መምህራንም በአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርተው ተቃውሞን የመሩትን እንዲያጋልጡ …

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጸረ ሽብር ግብረሀይል  ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላላፈው መልእክት አልሸባብና በኤርትራ የሚደገፉ ሀይሎች በመላው አገሪቱ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጁ መሆኑን አስተማማኝ መረጃ ደርሶኛል ብሎአል። ዜጎች እራሳቸውን ለመከላከል አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውም ገልጿል። ሰሞኑን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ፍተሻዎች ሲደረጉ የሰነበቱ ሲሆን፣ የትናንቱ ማስጠንቀቂያም ይህን ተከትሎ የተሰጠ ነው። መንግስት በኤርትራ የሚደገፉ የሽብር …

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ደንብ ቁጥር 250/2003 ሽሮ እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀ ፤ ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ የሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን ለማቋቋሚያ የወጣው አዋጅ ሀሙስ ይጸድቃል።በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ተዘጋጅቶ በካቢኔ ፀድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉ የትራንሰፖርት እና የኢንዱስትሪ የቁጥጥር ስርዓቶች ደህንነት ኮምፒዩተርን መሰረት …

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ እንደዘገበው በ2004 በጀት ዓመት ባልተሟላ ሰነድ ከ3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ባላይ ወጪ በማድረጉ በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ጠንካራ ትችት የቀረበበት የመከላከያ ሚኒስቴር የሒሳብ መዛግብቱን ዋናው ኦዲተርን ጨምሮ ለማንኛውም አካል ሚስጢር ማድረግ የሚያስችለውን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል። አዲሱ የመከላከያ ሠራዊት ረቂቅ አዋጅ ሰነድ በአንቀጽ 72 ንዑስ አንቀጽ …

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወጣት እስከ አዋቂ ያለው ከግማሽ በላይ የሚሆነው ኢትዮጵያ በልጅነቱ  በቂ ምግብ ሳያገኝ ተጎድቶ እንደሚያድግ የተመለከተው በኢትዮጵያ ይፋ በሆነው the cost of hunger in Ethiopia ጥናት ውስጥ ነው። 67 ከመቶ የሚሆነውና ከ15 አስከ 64 የእድሜ ክልል ውስጥ ያለው ኢትዮጵያዊ ጠንካራ ሰራተኛ ቢመስልም በልጅነቱ ያጣው የተመጣጠነ ምግብ አቀንጭሮትና አቀጭጮት …

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሾፈሮቹ ለኢሳት እንደገለጹት ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ የሚሄዱና   ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እቃዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ተፈትሸው ለማለፍ ረጅም ጊዜ እንደሚወስዱባቸው ተናግረዋል። ከ10 እስከ 15 ኪሎ ሜትር የሚደርስ የመኪኖች ሰልፍ መኖሩን የሚናገሩት ሾፌሮች፣ በጸሀይ ላይ በሚያደርጉት ጥበቃ በርካታ ሾፌሮች እየተጎዱ መሆኑንም ይገልጻሉ። ፍተሻው የተጀመረው ዛሬ አራት አመት ገደማ ቢሆንም፣ …

ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢው ፓርቲ መጪውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ለማክበር በጅጅጋ ከተማ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል። ለገዢው ፓርቲ ታማኞች ናቸው የተባሉና ” በተለምዶ ልማታዊ አርቲስትና ጋዜጠኞች እየተባሉ የሚጠሩ ታዋቂ ሰዎች አካባቢውን በመጎብኘት አድናቆታቸውን ሰጥተዋል። ኢሳት በክልሉ ያለውን ሁኔታ ከዘገበ በሁዋላ የተለያዩ ነዋሪዎች እና ጎብኝዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ክልሉን በቅርቡ አይታ …

ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከምሽቱ 7 አካባቢ አንድ የውጭ አገር ዜጋ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ጀርባው አካባቢ በጩቤ ተወግቶ መገደሉን ለማወቅ ተችሎአል። ግለሰቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኛ ሳይሆን አይቀርም። ግድያውን ማን እንደፈጸመውና ለምን እንደተፈጸመ የታወቀ ነገር የለም። የክልሉን ፖሊስ ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን የምናቀርብ መሆናችንን እንገልጻለን።

ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቀረበባቸውን የስም ማጥፋት ክስ ፍ/ቤት ቀርበው ምላሽ ለመስጠት ወደ ሐዋሳ ያመሩት የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ባልደረቦች ከደረሰባቸው የባጃጅ ተሸከርካሪ አደጋ ጋር በተያያዘ በተለይ ኤፍሬም በየነ ላይ የከፋ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ በመዋጮ ህይወቱን ለማትረፍ እየተደረገ ያለው ጥረት እስካሁን ውጤቱ አመርቂ አለመሆኑን አንድ የዕርዳታ አሰባሳቢ …

ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህወሀት በውስጡ የተነሳበትን መከፋፈል ለማስቀረት በእነ አቶ ስብሀት ነጋ የሚመራው ቡድን የቀድሞ ታጋዮችን በማሰባሰብ ህወሀትን ለማዳን በሚረባረብበት ጊዜ፣ በአቶ ስየ አብርሀ እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የተጀመረው ዘመቻ ግን እንደቀጠለ መሆኑ ታውቋል። አቶ ስየ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸው በእጅጉ የተገታ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ( ኢቲቪ) ” የነቀዙ ሀይሎች” በሚል በእርሳቸውና በአቶ …

ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሱዳን፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ መካከል በካርቱም የተካሄደው የአንድ ቀን ስብሰባ ያለውጤት ተጠናቋል። በኢትዮጵያና ግብጽ መካከል ልዩነቶች የተፈጠሩ ሲሆን፣ ልዩነቶችን ለማጥበብ ስለሚወሰደው እርምጃም አልተስማሙም። ብዙ ክብደት ተሰጥቶት የነበረው ስብሰባ በአንድ ቀን መጠናቀቁ በሁለቱ አገራት መካካል ያለው ልዩነት እየሰፋ መሄዱን የሚያሳይ ነው ተብሎአል። ምንም እንኳ ከአንድ ወር በሁዋላ አገራቱ …

ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በግብጽ የተቀሰቀሰን አመጽ ተከትሎ በወታደራዊ ሀይሉ ጣልቃ ገብነት ከስልጣን የተወገዱትና በእስር ላይ የሚገኙት መሀመድ ሙርሲ  በካይሮ ጉዳያቸውን እንዲያስችል በተሰየመው ፍርድ ቤት ቀርበው የግብጽ ፕሬዳንት መሆናቸውን ተናገሩ። ሙርሲ፦የተከሰሱበት መንገድ ህገወጥ መሆኑንና እርሳቸው የግብጽ ህጋዊ ፕሬዳንት ሆነው መቀጠል እንዳለባቸው ነው ለዳኞች የተናገሩት። እንደ ቢቢሲ  ሪፖርት ሙርሲና ሌሎች …

ጥቅምት ፳፭(ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት የውጭ መከላከያ ደህንነት እንዲሁም የህግ፣ ፍትህ እና የአስተዳደር ጉዳዩች ቋሚ ኮሜቴዎች አባላት ሰሞኑን እንዲወያዩበት በተደረገው የመከላከያ አዋጅ 98 በመቶ የሚሆኑት ወታደራዊ አዛዦች ከአንድ ብሄር የሆኑበትን አወቃቀር እንደማይለውጠው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው መኮንኖች ተናግረዋል: የመከላከያ ሚኒስቴር ሹሞች በበኩላቸው አዋጁ እስከ ዛሬ የነበሩትን ህጎች ሁሉ የሚለውጥና …

ጥቅምት ፳፭(ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ጋዜጠኞች እና በፖለቲካ ታማኝነት ተሹመው በሚያገለግሉ መሪዎች መካከል መተማመን የለም ሲሉ ጋዜጠኞች ለኢሳት ተናግረዋል፡፡ በጋዜጠኞች እና በአመራሩ መካከል ለተፈጠረው ልዩነት በርካታ ምክንያቶች ቀርበዋል። ጋዜጠኞቹ ለክልሉ ቴሌቪዥን ስርጭት ልዩ ምልክት ወይም ሎጎ ሁኖ እንዲያገለግል የተመረጠው የሰማእታት ሃውልት አርማ የአማራን ህዝብ የሚወክል አይደለም በማለት ተቃውሞ እያሰሙ ነው፡፡ …

ጥቅምት ፳፭(ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላው ኢትዩጵያ ተግባራዊ እንዲደረግ በኢህአዴግ ጽ/ቤት በኩል ለ14 ቀናት የሚቆይ ሰልጠና ተቀርጾ ወደ ታች በመውረድ ተግባራዊ እየተደረገ ነው፡፡ ቅድሚያ እንዲያስተገብር ትዕዛዝ የተላለፈለት የአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች ስልጠናውን እየሰጠ ነው። ስልጠናው የኢትዩጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ  ወይም ኢህአዴግ የተጋድሎ ታሪክ  ላይ የሚያተኩር ሲሆን አርሶ አደሮች በኢህአዴግ …

ጥቅምት ፳፭(ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ ግንባታ ዘርፍ በየጊዜው እየናረ የመጣው የግብአቶች ዋጋ ንረት በተለይ በብድር የሚሰሩ በርካታ ግንባታዎችን እያስተጓጎለ እንደሚገኝ ታውቋል። ከመንገዶች ባለስልጣን የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው የግንባታ ግብአቶች ዋጋ ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ ከ100 እስከ 237 በመቶ የዋጋ ንረት አሳይቶአል፡፡ መረጃው እንደአብነት ከዘረዘራቸው ግብአቶች መካከል ነዳጅ እ.ኤ.አ በ2009 ዓ.ም በሊትር 7.13 ብር የነበረው …

ጥቅምት ፳፪(ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድ ከወረዳ ጀምሮ ያሉ አባላቱን እየገመገ ሲሆን፣ ግምገማው በእርስ በርስ ሽኩቻና መጠላላፍ እየተካሄደ ነው። ከድርጅቱ አመራሮች መካከል አንዱ ለኢሳት እንደገለጹት ድርጅቱ ህልውና አደጋ ውስጥ ወድቋል።የዝምድና አሰራር እንዲሁም በቡድን ተደራጅቶ አንዱ ሌላውን የሚያጠቃበት ሁኔታ በሰሞኑ ግምገማ በስፋት የታየ ሲሆን፣ አብዛኛው ከታች እስከ ላይ ያለው …

ጥቅምት ፳፪(ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፉ የገንዘብ ተቋም ባወጣው የ2004-2005 ግምገማ ኢትዮጵያ ድህነትን ለመቅረፍ የምታደርገውን ጥረት አድንቋል። በኢኮኖሚው ረገድ ስኬት እየታየ መሆኑን፣ አገሪቱም የ7 በመቶ እድገት ማስመዝገቡዋን የገለጸው አይ ኤም ኤፍ፣ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር መንግስት የወሰደውን እርምጃንም አድንቋል። የአቶ መለስ ሞት በፈጠረው መደናገጥ ሁሉም የውጭ ምንዛሬ ለመግዛት መገደዱን በዚህም ሳቢያ የተፈጠረው የምንዛሬ …

ጥቅምት ፳፪(ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክልሉ ለረጅም አመታት ኖረው በተለያዩ ምክንያቶች ከአካባቢው እንዲለቁ የተደረጉ አንዳንድ ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት ፣ መስተዳድሩ እንኳንስ የሌሎችን አካባቢዎች ህዝብ መብት ለማክበር ቀርቶ የክልሉን ነዋሪዎች መብት ማክበር አልቻለም ብለዋል። ከሌላ ክአካባቢዎች የመጡ በተለይም የአማራ ተወላጆች ሶማሊያ መናገር አትችሉም እየተባሉ ከስራ መባረራቸውን የገለጹት እኝህ ነዋሪዎች፣ በንግድ ስራ የሚተዳደሩና በጅጅጋ …

ጥቅምት ፳፪(ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ሌተናንት ጄኔራል ሆነው የተሾሙት በሱዳን የሚገኘውን እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር በመሆን  በጸጥታ መስከበር ስራ ላይ የተሰማራውን የኢትዮጵያ ጦር የሚመሩት ምናልባትም ጀኔራል ሳሞራ የነሱን ሊተኩ ይችላሉ የሚባሉት ሌተናንት ጀኔራል ዮሀንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያም በአዲስ አበባ የገነቡዋቸው የንግድ ህንጻዎች በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዋጋ እንደሚያወጡ ለእርሳቸው ቅርብ የሆኑ ሰዎች …

ጥቅምት ፳፪(ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀኪሙላ መሱድ የሚባለው የፓኪስታን ታሊባን መሪ የተገደለው በአሜሪካ ሰው አልባ የጦር ጅቶች መሆኑን አለማቀፍ ሚዲያዎች ቢዘግቡም እስካሁን ከአሜሪካ መንግስት በኩል የተሰጠ ማረጋገጫ የለም። ግለሰቡ በአሜሪካ ከሚፈለጉ አሸባሪዎች ማካከል አንዱ ነው። አሜሪካ ግለሰቡ ያለበትን ለጠቆመ 5 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብታ ነበር። የመሱድ ምክትል ባለፈው ግንቦት ወር በተመሳሳይ …

ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክንያቱ በውል ባይታወቅም ካለፉት 4 ቀናት ጀምሮ በከተማዋ ከፍተኛ ፍተሻ እየተካሄደ እንደሆነ የዘጋብያችን መረጃ ያመለክታል። በተለይ ዛሬ በከተማዋ መውጫና መግቢያ በሮች ላይ ሰዎች ከመኪናዎች እና ባጃጆች ላይ እንዲወርዱ እየተደረገ በጥብቅ ተፈትሸዋል። አንዳንድ ወገኖች  መንግስት ጸረ ሰላም እና አሸባሪዎች በከተማዋ ገብተዋል የሚል ወሬ እንደሚያስወራ ሲገልጹ፣ ሌሎች ነዋሪዎች ደግሞ …

ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓመት 50ሺ የኮንዶምኒየም ቤቶችን ለመገንባት የያዘው ዕቅድ ከባድ ትችትን ያስከተለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዓመት ከ 100ሺ በላይ የቤቶች ግንባታ ለማከናወን ፊቱን ወደቻይና ኩባንያዎች ማዞሩ ተሰማ፡፡ አስተዳደሩ ከ800ሺ በላይ የኮንዶምኒየም ፣ ከ 136 ሺ በላይ የ40 በ60 ቤት ፈላጊ ነዋሪዎችን የመዘገበ ሲሆን ከዚህ ፍላጎት ጋር በማይጣጣም መልኩ …

ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በከፍተኘው ፍርድ ቤት ባለው የአስተዳደር ቊንጮ ማለትም በዋናው ፕሬዚዳንት በዳኛ ውብሸት ሽፈራውና በምክትሉ ማሃል ያለው አለመስማማት እየጨመረ በመሄዱ የፍርድ አሰጣጥ ሂደቱን እያበላሸው መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ገለጹ ። አሁን ባለው አሰራር ተሰሚነት ያለው የኢሃዴግ አባል የሆነው ምክትሉ ሲሆን ፣  ፕሬዘዳንቱ የኢሃዴግ አባል ባለመሆኑ ተሰሚነት አጥቷል ይላሉ …

ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዱስ ሲኖዶሱ ሰሞኑን ሲያደርግ የነበረውን ምልዓተ ጉበኤ ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ፣ በውጭ አገር ከሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋር ተጀምሮ የነበረው እርቀ ሰላም ወደ ፊት እንዲቀጥል እና ቤተክርስቲያን አንድነት እንዲጠናከር ወስኗል። የኦሮቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ቆጠራ እንዲካሄድና  የቤተክርስቲያኒቷ ታሪክ በደንብ ተጠንቶ እንዲቀርብም ወስኗል። ከፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ተወክለው የመጡ …

ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ እና በአማራ ክልሎች ያሉ አርሶ አደሮቹ ለኢሳት እንደተናገሩት ውጤታማ ባልሆኑበትና በግዴታ እንዲገዙ በተጠየቁት የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ እዳ እየተዋከቡ ነው። እዳችንን መክፈል አልቻንም የሚሉት አርሶ አደሮች መንግስት መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል። ግብርና ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ የዋለውን ዳፕ የተባለውን ማዳበሪያ ውጤታማ አልሆነም በሚል እንደሚቀይር ማስታወቁ ይታወቃል። …

ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቁም ነገር አዘል በሆኑ ቀልዶቹ የሚታወቀው ኮሜዲያን አብረሀም ከጀርባ ህመም ጋር በተያያዘ ሲሰቃይ ቆይቷል። ከጥቂት ወራት በፊት ወደ አውሮፓ በመምጣት በጀርመን አገር ህክምናውን ተከታትሎአል። አብርሀም በማእደ ኢሳት ዝግጅት ላይ ቀርቦ ለኢትዮጵያ ህዝብና የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ የረዱትን ወገኖች ማመስገኑና ጤናውም መሻሻልእያሳየ እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል ፡፡ ከዲስከ መንሸራተት ጋር  …

ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሪፖርተር ዛሬ ባወጣው ዘገባ በአገሪቱ የሚገኙ ሶስቱ ታላላቅ ስሚንቶ ፋብሪካዎች በአመት 12 ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ የማምረት አቅም ቢኖራቸውም በገበያ ውስጥ የሚገኘው ስሚንቶ ድምር ከ5 ሚሊዮን አይበልጥም። አብዛኛውን ስሚንቶ የሚገዛው መንግስት ሲሆን፣ የግሉ ዘርፍ ድርሻ ቀዝቃዛ መሆኑ ተዘግቧል። የሼክ ሙሀመድ አላሙዲን ንብረት የሆነው ደርባን ኩባንያ የዋጋ ቅናሽ በማድረግ በኩንታል …

ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጥሬ ቆዳና ሌጦ ኤክስፖርት ባለፉት አምስት ዓመታት የተሻለ ገቢ ያስገኘ ቢሆንም ግብይቱ ኃላቀር፣ሰንሰለቱ የተንዛዛና ከፍተኛ የግብይት ወጪዎች የሚታዩበት እንዲሁም በምርት ጥራት በኣለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱ እጅግ አነስተኛ መሆኑን ከንግድ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ አመለከተ፡፡ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ኤክስፖርትን በማቆም እሴት የተጨመረባቸውን የተለያዩ የቆዳ ውጤቶች ለውጪ ገበያ በመላክ የተሻለ የውጪ …