አቃቂ ብረታ ብረትን የገዛው ድርጅት የ34.9 ሚሊዮን ብር ክስ ቀረበበት

የአቃቂ ብረታ ብረት ፋብሪካን በጨረታ የገዛው ባዘቶ ኢንዱስትሪና ንግድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በገባው ውል መሠረት ክፍያ አልፈጸመም በሚል፣ የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የ34.9 ሚሊዮን ብር ክስ መሠረተበት፡፡