‹‹የአቡነ ጳውሎስ ፋውንዴሽን›› ለማቋቋም ታስቧል
- የአንደኛ ዓመት መታሰቢያ ሥነ ሥርዐት ነገ ይካሄዳል
- የቤተ ሰዎቻቸው የንብረት ይገባናል ጥያቄ ውሳኔ አላገኘም
- በ1.5 ሚልዮን ብር ጨረታ የተሰጠው የመቃብር ሐውልታቸው አልተሠራም
- ለ፳ኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸው “የካንሰር፣ ቲቢና ኤድስ የሕክምናና ማገገሚያ ማእከል” ግንባታን እንደ ስጦታ ያበረከተው ‹‹ራእይ ለትውልድ›› እና በዓል አድማቂዎቹ ‹‹ዉሉደ ጳውሎስ›› የት ናቸው?
አምስተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንደኛ ዓመት መታሰቢያ ነገ፣ ነሐሴ ፲ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በማሕሌት፣ በጸሎተ ፍትሐት እና በቅዳሴ ታስቦ ይውላል፡፡
በመታሰቢያ ሥነ ሥርዐቱ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና ድርጅት ሓላፊዎች፣ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናትና መዘምራን እንደሚገኙ ተገልጧል፡፡
