‹‹የአቡነ ጳውሎስ ፋውንዴሽን›› ለማቋቋም ታስቧል

  • የአንደኛ ዓመት መታሰቢያ ሥነ ሥርዐት ነገ ይካሄዳል
  • የቤተዎቻቸውንብረት ይገባናል ጥያቄ ውሳኔ አላገኘም
  • 1.5 ሚልዮን ብር ጨረታ የተሰጠ የመቃብር ሐውልታቸው አልተሠራም
  • ለ፳ ዓመት በዓለ ሢመታቸው “የካንሰር፣ ቲቢና ኤድስ የሕክምናና ማገገሚያ ማእከል” ግንባታን እንደ ስጦታ ያበረከተው ‹‹ራእይ ለትውልድ›› እና በዓል አድማቂዎቹ ‹‹ዉሉደ ጳውሎስ›› የት ናቸው?

The Late Patriarch Abune Paulos 1st Anniv.

አምስተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንደኛ ዓመት መታሰቢያ ነገ፣ ነሐሴ ፲ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በማሕሌት፣ በጸሎተ ፍትሐት እና በቅዳሴ ታስቦ ይውላል፡፡

በመታሰቢያ ሥነ ሥርዐቱ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና ድርጅት ሓላፊዎች፣ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናትና መዘምራን እንደሚገኙ ተገልጧል፡፡