ልጁን አስገድዶ የደፈረው አባት ከ44 ዓመት በላይ እስራት ተፈረደበት

የፌዴራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሰባተኛ ወንጀል ችሎት ሰኔ 22 ቀን 2003 ዓ.ም. በዋለው ችሎት፣ የ15 ዓመት ዕድሜ ያላትን ልጁን ደፍሮ ባስረገዘ የ48 ዓመት ዕድሜ ያለው ጌቱ መንዲዳ በተባለ ግለሰብ ላይ፣ የአርባ አራት ዓመት ከዘጠኝ ወራት ፅኑ እስራት ቅጣት አስተላለፈ፡፡