ሁለት መንግሥታዊ ተቋማት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንን ሊከፋፈሉት ነው

– ለ2003 የበጀት ዓመት 12.9 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለታል

(በውድነህ ዘነበ)

በመስከረም 2003 ዓ.ም. ይፋ በሚደረገው የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች መዋቅር፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በሁለት መንግሥታዊ ተቋማት ሥር እንደሚደራጅ ታወቀ፡፡