የጀርመን የጥንድ ዜግነት ደንብ

ከ2 ሳምንት በፊት በጀርመን የውጭ ዜጎች ድርብ ዜግነት እንዲይዙ የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ለጀርመን ፓርላማ ቀርቦ ነበር ። ይሁንና በፓርላማው አብላጫ ድምፅ ያላቸው ወግ አጥባቂዎች ለረቂቁ ድምፅቸውን ባለመስጠታቸው ሕጉ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል ። ዋነኛው ተቃዋሚ የጀርመን ሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ ና የአርንጓዴዎቹ ፓርቲ የረቂቁ ደጋፊዎች ናቸው ።