የኢትዮጵያ ትንሣኤ
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሃገሬ)
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (ኦ.ኤ.ዩ.) የአፍሪካ ሕብረት (ኤ.ዩ. በየአፍሪካ አንድነትን የተካው) ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ የወርቅ ኢዩቤልዩውን በማክበር ላይ ነው። በሜይ 1963 አፍሪካ አንድነት ሲመሰረት፤የጋናው ፕሬዝዳንት ክዋሚ ንኩርማ የመዝጊያ ንግግሩን የደመደመበት በተለይ በእድገት ላይ ያለችውንና ተቀኚ የነበሩትን የአፍሪካ ሃገራት ወደ ነጻነት ለመራችው ኢትዮጵያ ለክብሯ በመረጠውና ባዘጋጀው ግጥሙ ነበር።