አዲሱ የኢጣልያ ጠ/ሚኒስትር የአዉሮጳ ጉብኝት

አዲሱ የኢጣልያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤንሪኮ ሌታ የሁለቱን የኢጣልያ ምክር ቤቶች ይሁንታ ጠይቀዉ እጎአ ከ1948 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥምር መንግሥት መስርተዋል። ሌታ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ስልጣን እንደያዙ ጀርመንን ፈረንሳይን እና የአዉሮጳ ህብረትን በመጎቭኘት ላይ ናቸዉ።