የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ዘገባ

የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን በአባል ሀገራት ውስጥ የሚፈፀመውን ሕገወጡን የሰዎች ዝውውር ወንጀል የሚያጋልጥ ዘገባ በትናንቱ ዕለት በይፋ አወጣ። ዘገባው የ 2008፣ 2009 እና የ2010 ዓም መረጃዎችን መሠረት የተጠናቀረ ነው። በነዚሁ ሦስት ዓመታት ውስጥ ብቻ በጠቅላላ 23,600 ሰዎች የወንጀለኞቹ ሰለባ በመሆን፣ ለባርነት ሕይወት ተጋልጠዋል።