የመኾኖ ነዋሪዎች አቤቱታና የአስተዳደሩ መልስ

ነዋሪዎቹ ቤቶቹ ህጋዊ ናቸው ቢሉም የወረዳው መስተዳድር ግን በህገ ወጥ መንገድ መሰራታቸውን አስታውቋል ። የአካባቢው አስተዳደር ቤቶቹ የሚፈርሱት ለእርሻ የተሰጡና ለአዲስ ጎጆ ወጪዎች የተያዙ መሬቶች ተሸጠው በህገ ወጥ መንገድ ለቤት መሥሪያነት በመዋላቸው ነው ይላል ።