የብሪክስ ጉባኤ ፍፃሜና ተቃውሞው

5 ቱ የብሪክስ አባላት ብራዚል ሩስያ ህንድ ቻያናና ደቡብ አፍሪቃ ለባንኩ ለታቀደው መነሻ ካፒታል 50 ቢሊዮን ዶላር እኩል ድርሻ እንደሚያዋጡ ተገልጿል ። ይሁንና የብሪክስ ጉባኤን በመቃወም በተጓዳኝ በተካሄደ ሌላ ጉባኤ ደቡብ አፍሪቃ በብሪክስ ቡድን ውስጥ የምትጫወተውን ሚናና የጋራ ባንኩን የማቋቋሙ እቅድ ተተችቷል