ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኃይል መቆራረጥን ለማስቀረት መንግሥት ትኩረት ይሰጣል አሉ

-    ኢትዮጵያ ከነፋስ ኃይል 1.3 ሚሊዮን ሜጋ ማመንጨት እንደምትችል ተጠቆመ
-    ለአዳማ ሁለት ፕሮጀክት ብድር ተገኘ

በቃለየሱስ በቀለ

በተለያዩ ወቅቶች የሚከሰቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጦችን ለማስቀረት፣ መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡