የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ 2000 አውቶብሶች እንደሚያስፈልጉ ተገለጸ

ኅብረተሰቡ በከፍተኛ የትራንስፖርት እጥረት እየተንገላታ ነው

በታምሩ ጽጌ

ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ የነዋሪዎችና የትራንስፖርት አቅርቦቱ ተጣጥሞ እንደማያውቅ የሚነገርላት የአዲስ አበባ ከተማ፣ በተለይ በአሁኑ ጊዜ የከተማዋን መስፋትና የነዋሪዎችን ብዛት ተከትሎ የተከሰተውን እጥረት ለመፍታት 2000 አውቶብሶች እንደሚያስፈልጉት፣ የአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡