ጨለማው ሰው
ቴዎድሮስ ኃይሌ
በርካታ የኢትዮጵያውያን ድረ ገጾች (ኢንተርኔቶች) አሉ፣ በርካታ የኢትዮጵያውያን የፓልቶክ መነጋገሪያ ክፍሎች (ፓልቶክ ሩምስ) አሉ፣ በርካታ የኢትዮጵያውያን ሬዲዮ ጣቢያዎችና ጋዜጦች አሉ። የድረገጾቹን አዘጋጆች እናውቃቸዋለን – እዚያ ላይ አስተያየትና መጣጥፍ የሚያቀርቡትን ብዙዎቹን ግን አናውቃቸውም። ብዙዎቹን የፓልቶክ ውይይት ክፍል አስተዳዳሪዎች (አድሚንስ) እናውቃቸዋለን – እዚያ ላይ መጥተው የሚያወሩትንና አስተያየት የሚሰጡትን ብዙዎቹን ግን አናውቃቅቸውም።