ጨለማው ሰው

ቴዎድሮስ ኃይሌ

በርካታ የኢትዮጵያውያን ድረ ገጾች (ኢንተርኔቶች) አሉ፣ በርካታ የኢትዮጵያውያን የፓልቶክ መነጋገሪያ ክፍሎች (ፓልቶክ ሩምስ) አሉ፣ በርካታ የኢትዮጵያውያን ሬዲዮ ጣቢያዎችና ጋዜጦች አሉ። የድረገጾቹን አዘጋጆች እናውቃቸዋለን - እዚያ ላይ አስተያየትና መጣጥፍ የሚያቀርቡትን ብዙዎቹን ግን አናውቃቸውም። ብዙዎቹን የፓልቶክ ውይይት ክፍል አስተዳዳሪዎች (አድሚንስ) እናውቃቸዋለን - እዚያ ላይ መጥተው የሚያወሩትንና አስተያየት የሚሰጡትን ብዙዎቹን ግን አናውቃቅቸውም።