አቶ በረከት በሰንደቅ ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት ላይ

አቶ በረከት ስምኦን Bereket Simonግርማ ካሳ

አቶ በረከት ስምኦን አገር ውስጥ ለሚታተም የሰንደቅ ጋዜጣ የሰጡትን አስተያየት አውራምባ ታይምስ ድህረ ገጽ ላይ ተለጥፎ አነበብኩት። የተለዩ በረከት ስምኦንን አላነበብኩም። ያው ድሮም የምናውቃቸው በረከት ስምኦን ናቸው፤ ብስለትና ትህትና የጎደላቸው፣ በሚቃወሟቸው ወገኖች ላይ የሚያከሩ።