በሙኒክ ኦሎምፒክ የተገደሉት እስራኤላውያን መታሰቢያ

በሚኒክ ከተማ ይካሄድ በነበረው የኦሎምፒክ ውድድር ተሳታፊ በነበሩ የእስራኤል ስፖርተኞች ላይ በታጣቂ ፍልስጤማውያን በተሰነዘረ ጥቃት 11 ስፖርተኞች የተገደሉበት 40ኛ አመት ዛሬ በጀርመን ታስቧል ። ከሙኒክ በስተምእራብ በሚገኘው ፍዩርስተንፌልድብሩክ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር የጥቃቱ ሰለባዎች ታስበዋል።