ያለ ጨረታ! ለነ ሌንጮ ለታ?

እንግዳ – ከኦስሎ

መቸም! ተስፋዬ ገብረአብ በጥሩ ብዕሩ እያዋዛ በሚለቃቸው መጣጥፎቹ ውስጥ በየመስመሮቹ መሃል ወሸቅ የሚያደርጋቸው አፋጀሽኝ ቃላቶቹ አሁንም አልለቀቁትም። ”ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም” ሆነና አድባር ስትከፍትለ’ት በሚለቃቸው መጣጥፎቹ መስመሮች ውስጥ – በአብዛኛው በአማራና – ኦሮሞ ህዝብ ውስጥ ንትርክ እንዲቀጥል ሲፈልግ፣ ዛሬ ደግሞ ሴሜቲኮችና ኩሺትኮች በሚላቸው ኢትዮጵያውያን መሃል ሽኩቻው እንዳያባራ – የአበሻን – ተንኮል አሳምረው ሌንጮና ዲማ ያውቁታል በሚል ጥርጣሬው እንዲጠጥር በር ይከፍታል። ይህች አንጓ አስታራቂ ናት ወይስ ቀጣይ ጥርጣሬን ጫሪ? ደራሲ ተስፋዬ?