ያለ ጨረታ! ለነ ሌንጮ ለታ?

እንግዳ - ከኦስሎ

መቸም! ተስፋዬ ገብረአብ በጥሩ ብዕሩ እያዋዛ በሚለቃቸው መጣጥፎቹ ውስጥ በየመስመሮቹ መሃል ወሸቅ የሚያደርጋቸው አፋጀሽኝ ቃላቶቹ አሁንም አልለቀቁትም። ”ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም” ሆነና አድባር ስትከፍትለ’ት በሚለቃቸው መጣጥፎቹ መስመሮች ውስጥ - በአብዛኛው በአማራና - ኦሮሞ ህዝብ ውስጥ ንትርክ እንዲቀጥል ሲፈልግ፣ ዛሬ ደግሞ ሴሜቲኮችና ኩሺትኮች በሚላቸው ኢትዮጵያውያን መሃል ሽኩቻው እንዳያባራ - የአበሻን - ተንኮል አሳምረው ሌንጮና ዲማ ያውቁታል በሚል ጥርጣሬው እንዲጠጥር በር ይከፍታል። ይህች አንጓ አስታራቂ ናት ወይስ ቀጣይ ጥርጣሬን ጫሪ? ደራሲ ተስፋዬ?