ደጉ ኢትዮጵያዊ፤ ከልብ ካለቀሱ እምባ እንደማይገድ ያስመሰከረ ስብስብ
BefeQadu Z Hailu
Tagged with addis ababa, Amharic, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
![]() |
|
የዓለም ደቻሳልጆች፣ ባለቤት (መሃል) እና ወንድም (በስተቀኝ)
|
“አለቀለት ሲባልፍቅር ተሙዋጠጠ
የፌስቡክ ዝምድና ነገርንለወጠ::” ~ Bizu Hiwot
“ፌስን ቡክአድርገው የተቀጣጠሩ
በልብ መነጽር ገጹንያነበቡ
ሸበሌ ከትመው ታሪክአስከተቡ፡፡” ~ Desu Aragaw
እነዚህ ግጥሞች የተገጠሙት ‹ደጉ ኢትዮጵያዊ› ላዘጋጀውየዓለም ደቻሳ ቤተሰብ ገቢ ማሰባሰቢያ የስነጽሁፍ ምሽት ለተገኘው የመጀመሪያ ስኬት፣ በፌስቡክ ላይ ነው፡፡ ወደስኬቱ በኋላ ላይየምንመለስበት ቢሆንም መጀመሪያ ‹ደጉ ኢትዮጵያዊ› ምንድን ነው፣ ማነው፣ ከየት ነው፣ ወዴት ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች በአጭሩ እንመልስ፡፡
‹ደጉ ኢትዮጵያዊ› ከዚህ በፊት በአካል የማይተዋወቁ 16 የፌስቡክ ጓደኛሞችየፈጠሩት የፌስቡክ ቡድን ነው፡፡ የደጉ ሳምራዊን ታሪክ መነሻ አድርጎ÷ በሊባኖስ መንገድ ላይ እየተጎተተች መኪና ውስጥእንደትገባ ከተደረገች በኋላ በማግስቱ ራሷን አጥፍታለች የተባለችውን ዓለም ደቻሳ ቤተሰቦች የእዝን ለመስጠት እና እግረ መንገዱንምስለጉዳዩ አሳሳቢነት አነስተኛ ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ለማዘጋጀት የተመሰረተው ‹ደጉ ኢትዮጵያዊ› ምንም እንኳን ሕጋዊሰውነት የሌለው ቡድን ቢሆንም በበጎ ፈቃደኝነት መስራት የሚፈልጉትን መስራቾቹን እና በፌስቡክ በተከፈተው የቡድኑ ገጽ ውስጥበገቡ ከ4,000 በላይ አባላቶቹ ድጋፍ የሚከተሉትን ዓላማዎች ግብ አድርጎ ለመንቀሳቀስ ሕልም አለው፡፡
-
የ‹ደጉ ኢትዮጵያ› ቡድን አባላትን ስለቤት ሰራተኞች መብት፣ ጥቃት እና ሌሎችም ነባራዊሁኔታዎች መሰረታዊ ግንዛቤ ማስጨበጥ፡፡
-
ከፍተኛ ጥቃት የሚፈፀምባቸውን የቤት ሰራተኛ ተቀባይ ሃገራትን/መዳረሻዎችን ለይቶ ማወቅእና ማሳወቅ፡፡
-
ትኩረት ወደሚደረግባቸው መዳረሻ ሃገራት በርካታ የቤት ሰራተኞችን ከሚልኩ ወኪሎች (ኤጀንቶች)ጋር ዘላቂ ግንኙነት መፍጠር፡፡
-
ከየትኛው የኢትዮጵያ ክልል በርካታ ሴቶች ለቤት ሰራተኝነት እንደሚሰደዱ ለይቶ በማወቅግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መስራት፡፡
-
‹የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ› የተባለ የግንኙነት መረብ የቤት ሰራተኛ ተቀባይ በሆኑ መዳረሻሃገራት ውስጥ መመስረት እና መሰረታዊ መረጃ እና ድጋፍ መለዋወጥ፡፡
‹ደጉ ኢትዮጵያዊ› ትላንት ምን ሠራ?
ደጉ ኢትዮጵያዊ፣ ትላንት ሚያዝያ 11፤ 2004 በዋቢ ሸበሌ ሆቴል አዳራሽየስነጽሁፍ ምሽት ያዘጋጀ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ወደ 400 የሚጠጉ ሰዎች መገኘታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ገቢው ሙሉ ለሙሉ ለዓለምደቻሳ ቤተሰቦች በባለቤቷ እና በወንድሟ ስም በተከፈተ አካውንት ገቢ የሚደረግ የመግቢያ ትኬት የተሸጠ ሲሆን፣ ታዳሚዎች እንደየፍላጎታቸውባለ 25፣ 50 ወይም 100 ብር ትኬት እየገዙ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ ዋቢሸበሌ ሆቴልን ጨምሮ በርካታ ድርጅቶች እና ግለሰቦችድጋፋቸውን ያደረጉ በመሆኑ ዝግጅቱን ለማካሄድ ምንም ወጪ አላስፈለገም ማለት ይቻላል፡፡
ፕሮግራሙ መጀመሪያ ላይ የሳውንድ ሲስተም መንገራገጭ ከመጋፈጡ በቀር በስኬትተካሂዷል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ በርካታ አንጋፋእና አማተር ገጣሚያን ግጥሞቻቸውን ያነበቡ ሲሆን፣ የ10 ደቂቃ ዶኩመንተሪ፣ የደጉ ኢትዮጵያ ቡድን ማስተዋወቂያና አጭር ምክርበአቶ በኃይሉ ገ/መድህን ተደርጓል፡፡ አንዱአለም ተስፋዬም የዳንኤል ክብረትን ጽሁፍ ያነበበ ሲሆን መድረኩን ሜሮን ጌትነትመርታዋለች፡፡ ሙኒት እና ዮርግ ታዳሚውን ለማዝናናት የተገኙ የነበረ ቢሆንም በሳውንድ ሲስተሙ ላይ በተከሰተው ችግር ምክንያት፣ዮርግ ጊታሩን ባይጫወትም ሙኒት ‹‹አስታውሳለሁ፣ መች እረሳለሁ›› የሚለውን ዜማ በታዳሚው ታጅባ ተጫውታለች፡፡ ከሌሎችም በርካታየተጋበዙ እንግዶች መካከል የዓለም ደቻሳ ባለቤት፣ ወንድሟ እና ሁለት ልጆቿም እንዲገኙ ተደርጓል፡፡
በዕለቱ በር ላይ ከተሸጡት ትኬቶች ብቻ ከ16ሺኅ ብር በላይ የተገኘ ሲሆን÷ ዘግየትብሎ እንደሰማሁት ደግሞ በፋራናይት ላውንጅ እና ሌሎችም ቦታዎች ተቀምጦ ከነበረ ትኬት የተገኘው ገቢ ሲደማመር ወደ 20,000ብር ተጠግቷል፡፡ በተጨማሪም አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ግለሰብ የልጆቹን ሙሉ የትምህርት ወጪ÷ ትምህርታቸውን እስኪጨርሱድረስ ለመሸፈን ቃል ገብተዋል፡፡ ሌሎችም ግለሰቦች የተከፈተውን ባንክ አካውንት ቁጥር የወሰዱ ሲሆን የ‹ደጉ ኢትዮጵያ› ትልቅስኬት እንደሆነ የተነገረው ግን በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በፌስቡክ በተመሰረተ ቡድን አማካይነት ማሕበራዊ ፋይዳ ያለው ሥራመስራቱና በዚሁ መቀጠል የሚችልበትን ዕድል ለሁሉም ክፍት አድርጎ ማስተዋወቁ ላይ ነው፡፡
——
ከደጉኢትዮጵያ ጋር አብሮ ለመሥራት የሚፈልጉ ሰዎች በፌስቡክ ወይም በኢሜይል [email protected]መጻፍ እንደሚችሉአባላቱ ተናግረዋል፡፡
