ደጉ ኢትዮጵያዊ፤ ከልብ ካለቀሱ እምባ እንደማይገድ ያስመሰከረ ስብስብ
BefeQadu Z Hailu
Tagged with addis ababa, Amharic, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
![]() |
የዓለም ደቻሳልጆች፣ ባለቤት (መሃል) እና ወንድም (በስተቀኝ) |
“አለቀለት ሲባልፍቅር ተሙዋጠጠ
የፌስቡክ ዝምድና ነገርንለወጠ::” ~ Bizu Hiwot
“ፌስን ቡክአድርገው የተቀጣጠሩ
በልብ መነጽር ገጹንያነበቡ
ሸበሌ ከትመው ታሪክአስከተቡ፡፡” ~ Desu Aragaw
እነዚህ ግጥሞች የተገጠሙት ‹ደጉ ኢትዮጵያዊ› ላዘጋጀውየዓለም ደቻሳ ቤተሰብ ገቢ ማሰባሰቢያ የስነጽሁፍ ምሽት ለተገኘው የመጀመሪያ ስኬት፣ በፌስቡክ ላይ ነው፡፡ ወደስኬቱ በኋላ ላይየምንመለስበት ቢሆንም መጀመሪያ ‹ደጉ ኢትዮጵያዊ› ምንድን ነው፣ ማነው፣ ከየት ነው፣ ወዴት ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች በአጭሩ እንመልስ፡፡
‹ደጉ ኢትዮጵያዊ› ከዚህ በፊት በአካል የማይተዋወቁ 16 የፌስቡክ ጓደኛሞችየፈጠሩት የፌስቡክ ቡድን ነው፡፡ የደጉ ሳምራዊን ታሪክ መነሻ አድርጎ÷ በሊባኖስ መንገድ ላይ እየተጎተተች መኪና ውስጥእንደትገባ ከተደረገች በኋላ በማግስቱ ራሷን አጥፍታለች የተባለችውን ዓለም ደቻሳ ቤተሰቦች የእዝን ለመስጠት እና እግረ መንገዱንምስለጉዳዩ አሳሳቢነት አነስተኛ ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ለማዘጋጀት የተመሰረተው ‹ደጉ ኢትዮጵያዊ› ምንም እንኳን ሕጋዊሰውነት የሌለው ቡድን ቢሆንም በበጎ ፈቃደኝነት መስራት የሚፈልጉትን መስራቾቹን እና በፌስቡክ በተከፈተው የቡድኑ ገጽ ውስጥበገቡ ከ4,000 በላይ አባላቶቹ ድጋፍ የሚከተሉትን ዓላማዎች ግብ አድርጎ ለመንቀሳቀስ ሕልም አለው፡፡
የ‹ደጉ ኢትዮጵያ› ቡድን አባላትን ስለቤት ሰራተኞች መብት፣ ጥቃት እና ሌሎችም ነባራዊሁኔታዎች መሰረታዊ ግንዛቤ ማስጨበጥ፡፡
ከፍተኛ ጥቃት የሚፈፀምባቸውን የቤት ሰራተኛ ተቀባይ ሃገራትን/መዳረሻዎችን ለይቶ ማወቅእና ማሳወቅ፡፡
ትኩረት ወደሚደረግባቸው መዳረሻ ሃገራት በርካታ የቤት ሰራተኞችን ከሚልኩ ወኪሎች (ኤጀንቶች)ጋር ዘላቂ ግንኙነት መፍጠር፡፡
ከየትኛው የኢትዮጵያ ክልል በርካታ ሴቶች ለቤት ሰራተኝነት እንደሚሰደዱ ለይቶ በማወቅግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መስራት፡፡
‹የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ› የተባለ የግንኙነት መረብ የቤት ሰራተኛ ተቀባይ በሆኑ መዳረሻሃገራት ውስጥ መመስረት እና መሰረታዊ መረጃ እና ድጋፍ መለዋወጥ፡፡
