የአዋሊያ የእስልምና ተቋም ጥያቄ

በአዋሊያ የአስልምና ተቋም ፣በርካታ የሃይማኖቱ ተከታዮች፣ መንግሥት ጣልቃ ገብቷል፤ የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤት (መጅሊስ) በህዝብ የተመረጠ አይደለም በማለትና ሌሎች ጥያቄዎችንም በማንሣት፤ በተቃውሞ፤ በአዋሊያ መሥጊድ መሰብሰብ ከጀመሩ ከ 10 ሳምንታት በላይ አልፈዋል። መንግሥት በበኩሉ፣ ታደሰ እንግዳው በዘገባው ላይ እንዳመለከተው፤ በአክራሪነት የፈረጀው የወሃብዪ እምነት አራማጆች፤ በሃይማኖቱ ሽፋን ፍላጎታቸውን በሌላው ህዝብ ላይ በግድ ለመጫን የጀመሩት እንቅሥቃሤ አለ ነው የሚለው። መንግሥት፤ «ህገ-መንግሥታችን፤ ሸሪያችን ነው » የሚል ፀረ-ህገ-መንግሥት እንቅሥቃሴ አለ በማለት ማስረጃ መጥቀሱን የታደሰ ዘገባ በተጫማሪ ያስረዳል። ያዳምጡ