የአዋሊያ የእስልምና ተቋም ጥያቄ
በአዋሊያ የአስልምና ተቋም ፣በርካታ የሃይማኖቱ ተከታዮች፣ መንግሥት ጣልቃ ገብቷል፤ የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤት (መጅሊስ) በህዝብ የተመረጠ አይደለም በማለትና ሌሎች ጥያቄዎችንም በማንሣት፤ በተቃውሞ፤ በአዋሊያ መሥጊድ መሰብሰብ ከጀመሩ ከ 10 ሳምንታት በላይ አልፈዋል። መንግሥት በበኩሉ፣ ታደሰ እንግዳው በዘገባው ላይ እንዳመለከተው፤ በአክራሪነት የፈረጀው የወሃብዪ እምነት አራማጆች፤ በሃይማኖቱ ሽፋን ፍላጎታቸውን በሌላው ህዝብ ላይ በግድ ለመጫን የጀመሩት እንቅሥቃሤ አለ ነው የሚለው። መንግሥት፤ «ህገ-መንግሥታችን፤ ሸሪያችን ነው » የሚል ፀረ-ህገ-መንግሥት እንቅሥቃሴ አለ በማለት ማስረጃ መጥቀሱን የታደሰ ዘገባ በተጫማሪ ያስረዳል። ያዳምጡ
ያስቃል!! በ እውነት ያስቃል የሚያስቀው መንግስት ነው!
አዎ!የግብጹም መሪ እንዲህ ነበር ያሉት:በ እርግጥ የቱኒዚያው ቀድመዋል!ጋዳፊም አሸባሪዎች ናቸው ማለቱን እስከ ትንፋሹ መጨረሻ ሲናዘዝ ነበር :አሁንም የሶሪያው ሽብርተኞች ናቸው እያለ ነው:;
እኔ የምለው 200,000 ብቻ ተደርጎ የተቆጠረው የአዲስ አባባ ሙስሊም እንዴት 500,000 ሊሆን ቻለ?
አሁንብም የሙስሊሙ ጥያቄ አንድ እና አንድ ነው!መጅሊስ አይወክለንም!አህባሽ ከኢትዮጵያ ይጥፋ ወይም መንግስት ለአህባሽ የሚሰጠውን ድጋፍ ያንሳ የሚል ነው::
ይህ ካልሆነ ደግሞ ወደ ቀጣዩ ጥያቄ ይኬዳሎ::በነገራችን ላይ ወሃብይ ማለት መብቱን በሰላም የሚጠይቅ ማለት ነው!አልቃኢዳ ማለት ደግሞ በሰላም ያላገኘውን ጥያቄ እንደ ወያኔ በትጥቅ ትግል የሚጠይቅ ማለት ነው::ስለዚህ ሽንብራ እና ሽንቡራ ልዩነቱ ምንድን ነው ቢለው አፍማሞጥሞጡ ትርፍ ነው አለ ይባላል::
ጥያቄዎች በሰላም ይጠየቃሉ መንግስት ደግሞ እረብሻ እንዲነሳ ይገፋፋል!!!እናት ኢትዮጵያ ያንች መከራ የሚያበቃ ምቼ ይሆን?ሁሌ መዝገሮች ከጡትሽ ተጣብቀው አሰቃዩሽ!አንችም ሞኝ እና ተላላ መሆንሽ አልቀረም !የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ ነው የሚንቀባረር::ለሁሉም ግን ጊዜ አለው::
በነገራችን ላይ መንግስት በሙስሊሙ እምነት ጣልቃ ገብቶ አህባጭ የሚባል አስተምሮ ይሻላችኋል ማለቱ አያስደንቃችሁም?እውነት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመስገጃ ቦታ ስጡን ሂጃብ አትከልክሉን ከማለት በዘለለ ሁኔታ አስበው ያውቃሉ?
እርስዎስ ምን ይላሉ? ለማንኛውም መሪዎች በስልጣናቸው መገባደጃ ማግስት የሚያሰሙትን ኑዛዜ ይኸው ቅጥረኛ/አሸባሪ ህገ መንግስት አፍራሽ …. እያለ ይቀጥልና ትንፋሽ ሲቆም እንደጋዳፊ ሰጥ ይላል…ዳሩ ምን ያደርጋል ዛሬ በሰዎች ላይ ጣታችንን እየቀሰርን እኛም ከ እጅ አይሻል ዶማ ሆነን ነገ ከነሱ ብሰን ይቀሰርብናል………….ወያኔ ደርግን በጣልወ ማግስት ልብሱን ቀየረ!ቃሉንም ቀየረ !በቃሉ የጠና በአንድ ነገር ብቻ ነው ..ኤርትራን በማስገንጠል!!!