የትራፊክ አደጋን በግማሽ ለመቀነስ ያስችላል የተባለ ዕቅድ ይፋ ተደረገ

በመላው ኢትዮጵያ በየዓመቱ የሚደርሰውን 2,200 የሞት አደጋ፣ 8,000 የአካል ጉዳትንና ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የንብረት ውድመትን በግማሽ መቀነስ የሚያስችል፣ የ10 ዓመት የመንገድ ደኅንነት ስትራቴጂና የድርጊት መርሐ ግብር ተዘጋጅቶ ይፋ ተደረገ፡፡