የአላሙዲ ኩባንያ 5,000 ሰራተኞች ከፊሊፒንስ ወደ ኢትዮጵያ ሊያስመጣ ነው

ኃያል ዓለማየሁ | The Reporter

ከጥቂት ወራት በፊት የሚድሮክ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን የተረከበው በሚድሮክ ጥላ ሥር የሚገኘው ሜፖ የተባለው የሚድሮክ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ቢሮ፣ አምስት ሺሕ የፊሊፒንስ ዜጎችን ለመቅጠር ዝግጅት ማጠናቀቁን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡ የእነዚሁ የውጭ አገር ዜጎችን ቅጥርም በኢትዮጵያ ሠራተኞች ላይ ስጋት መፍጠሩን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ 350 የሚሆኑ የፊሊፒንስ ዜጎች የአፍሪካ ኅብረት በሚድሮክ ወይም በሜፖ የሚያስገነባውን ሆቴል ጨምሮ፣ በተለያዩ የሜፖ ፕሮጀክቶች ላይ ተሠማርተው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ቀደም ሲል የእነዚሁ በሜፖ ፕሮጀክቶች ላይ የተሰማሩ የፊሊፒንስ ዜጎች ቁጥር 400 ደርሶ እንደነበር የገለጹት ምንጮች፣ የተወሰኑት በቀን ሥራ ላይም ተመድበው ይሠሩ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ሜፖ እነዚህ አምስት ሺሕ የሚሆኑ በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ በዓለም ላይ የታወቁ የፊሊፒንስ ዜጎችን ለመቅጠር የወሰነው፣ በተለይ የአፍሪካ ኅብረት በቀድሞው ከርቸሌ በሚያሠራው ሆቴልና ሌሎች ፕሮጀክቶች በሚድሮክ ኮንስትራክሽን ሥር በነበሩበት ጊዜ እጅግ ተጓተው የነበሩ በመሆኑ፣ የፕሮጀክቶቹን ግንባታ ለማፋጠን እንደሆነ ታውቋል፡፡

ሜፖ የወሰደው ዕርምጃ አንዳንድ ሠራተኞች ላይ ከሥራ ህልውና ጋር በተያያዘ ስጋት መፍጠሩን የጠቆሙት ምንጮቻችን፣ እነዚሁ የፊሊፒንስ ዜጎች በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያውያን የሚሠሩዋቸውን የግንበኛ፣ የአናጢነትና የመሳሰሉትን ሥራዎች እየተቆጣጠሩ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ለእነዚሁ አምስት ሺሕ ለሚሆኑና በመላው በአገሪቱ በሚገኙት የሜፖ ፕሮጀክቶች ላይ ለሚሳተፉት ፊሊፒያውያን፣ ድርጅቱ ከኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በወሰደው ሰፊ ቦታ ላይ የመኖሪያ መንደር በማዘጋጀት ላይ መሆኑም ታውቋል፡፡

ይህንኑ ሁኔታ እንዲገልጹልን የሜፖ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለሆኑት ለሚስተር ባሲም አልዳኸር በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ በተመሳሳይም ጉዳይ የሚመለከታቸውን ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ኃላፊዎችን አግኝተን ለማናገር ያደረግነው ጥረት አብዛኛዎቹ በስምንተኛው የኢሕአዴግ ጉባዔ ላይ ተሳታፊ ስለነበሩ አልተሳካም፡፡

ሜፖ የተረከባቸውን ፕሮጀክቶች ለማቀላጠፍ አዳዲስ ማሽኖችና የግንባታ መሣሪያዎች በብዛት በማስገባት ላይ ይገኛል፡፡

በሚድሮክ ኮንስትራክሽን ሥር በነበሩበት ወቅት የተጓተቱትን በርካታ ፕሮጀክቶች ለማፋጠን፣ በውጭ አገር ዜጋ የሚመራው ሜፖ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ምንጮች ጠቅሰዋል፡፡

4 Comments on “የአላሙዲ ኩባንያ 5,000 ሰራተኞች ከፊሊፒንስ ወደ ኢትዮጵያ ሊያስመጣ ነው”

  1. wow, this story is very odd to me. Can not they train 40% of ethiopians who are unemployeed to do this job? The jobs they are talking about here are not rockt science. train the unemployeed and let them work.

  2. Out-sourcing is for the americans and the West, that is characteristics of the developed world. Here it is like in-sourcing cheap labour of philipino maids to the middle-east. It is not a sign of development. Most prominent, feudal arrogance and alienation.

  3. This is unacceptable ! 20 million Ethiopians are out of work. MEDROC should give these jobs to Ethiopians first. I will protest until I die for my people !

  4. ለአቶ አላሙዲ ይህን አጠር ያለ አስተያየት የምፅፈው ከቶሮንቶ ካናዳ ነው፡፡ ለመሆኑ አገርዎን ይወዳሉ? ? ? ለምን እንዲህ እንዳልኩኝ ቢያውቁ እነዚህ ፍሊፒን የሚባሉ ሰዎች አገራችን ሊገቡ ነው የሚለው ፅሁፍ በጣም አሰቅቆኝ ነው፡፡ እዚህ ቁም ስቅላችንን የሚያሳዩን አንሶ ደግሞ ሀገሬ ገብተው ህዝቤን ያሰቃዩ? እርስዎ ሲያስቡት የኛ አገር ሰው የተማረ ጠፍቶ ነው? ከአስፈለገስ ደግሞ ማሰልጠን አቅቶ ነው ወይ? እባክዎ በህዝብዎ፣ በአገርዎ፣ ላይ ገንዘብዎን ቢያጠፉ ይሻላል፡፡ በአንድ በኩል ያላዩት ነገር ቢኖር እነዚህ ፍሊፕኖች የሚያመጠት መጥፎ በህል፣መጥፎ መዳቀልን፣ እንዲሁም የወንድ ለወንድ እና የሴት ለሴት ጋብቻን የሚፈፅሙ ናቸው ለእነሱም ሆነ ለሌላ የውጭ አገር ሰው ይህንን የመሰለው ነገር ለአገሪቱ በጣም ጎጂ እንጂ ጠቃሚ እንዳልሆነ ቢረዱት ጥሩ ይመስለኛል፡፡ የእርስዎ አማካሪዎች የውጭ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ ታዲያ እነዚህ የውጭ ዜጎች ይህችን አገር በጥሩ የሚመለከቱት ይመስልዎታል እስቲ ለትንሽ ጊዜ ቁጭ ብለው ያስቡበት፡፡ ይህንንም የምለው ጊዜ እንደሌለ ይገባኛል ግን ይህ ለአንድ እናት ሀገር ነው፡፡እባክዎ እባክዎ በጣም ያስቡበት በአላህ በአላህ!!!!
    ለወደፊት ለታሪክ ጥሩ ነገርን ያድርጉ መቼም ሰው ሆኖ ከሞት የሚቀር የለም ሞቱን ያርቀውና እንዲህ አይነቱ ነገር ያጠያይቃል ሰዉ የወደደዎትን ያህል ሁሌም ስምዎ ሁሌም እንዳይኮነን አደራ አደራ!!! በድጋሚ በአገርዎ ሰው ላይ ትምህርት ቤት በመክፈት፣ ወጣቶችን በማስተማር፣ እነዚህን በመሳሰሉት ስምዎን በጥሩ እንዲጠራ ያድርጉ፡፡ የነዚህን የውጭ ሰዎች ነገር እባክዎ ያስቡበት ለሌሎችም ትምህርት ይስጡ፡፡ እንዲመጡም ተፈራርመው ከሆነ ማሰረዝ ይችላሉ፡፡ መርዝ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደመነስነስ ይቆጠራል እነሱ ገቡ ማለት አደራ አደራ የአገሬ ነገር በጣም ያንገበግበኛል፡፡ እንኳን 5000 ቀርቶ 5 ቢገቡ እንዴት በአንድ አመት ወስጥ 5000 እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም እበክዎት አደራ አደራ ከቶሮንቶ ካናዳ አገር ወዳድ ነኝ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*