ቅ/ሲኖዶስ: በመላው ገዳማት፣ አድባራትና የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ ዐወጀ::

ቅ/ሲኖዶስ: በመላው ገዳማት፣ አድባራትና የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ ዐወጀ፤

“ባሳለፍናቸው ሳምንታት ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖችን በመሪር ሐዘንና በጸሎት እናስባቸዋለን”

img294

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
ኅሡ ሰላማ ለብሔር እስመ በሰላመ ዚአሃ ይከውን ሰላምክሙ፤
(የአገርን ሰላም እሹ ፈልጉ የአገራችኹ ሰላም የእናንተ ሰላም ነውና)

 የተወደዳችኹ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

የሀገርና የወገን ፍቅር ያለው ሕዝብ ሰላም ከእግዚአብሔር መኾኑን ያውቃል፤ ሰላም ለሰው ልጆች ከማናቸውም መሠረታውያን ፍላጎቶች በላይ ተቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራችን የተለያዩ ሃይማኖቶች፣ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ተቻችለውና ተረዳድተው የሚኖሩባት የዓለም ምሳሌ ናት፡፡ ይህን ዓለምን የሚያስደንቅ ገጽታችንን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንዲከተለው ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የተወደዳችኹ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያውያት፤

ኢትዮጵያ አህጉረ ሰላም(የሰላም ሀገሮች) ከሚባሉት ከዓለም ሀገሮች አንዷ ስትኾን በአኹኑ ጊዜ በአንዳንድ ክልሎችና ከተሞች የሚታየው አለመረጋጋት ኹሉንም የሚያሳሳብ ኾኖ አግኝተነዋል፡፡

ከዚኽም ጋር ባለፍናቸው ሳምንታት በተከሠተው ያልተጠበቀ ችግር፡-

  1. በአንዳንድ አካባቢ የሰው ሕይወት ሲጠፋ፤ ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ፤ የንግድ ተቋማት፣ የሕዝብና የመንግሥት ንብረት ሲወድም፤ የሕዝባችን የዕለት ከዕለት ኑሮ ሲናጋ ኹሉም ኅብረተሰብ የችግሩ ተጠቂ ኾኗል፤ የዚኽ ዓይነቱ ድርጊት በዚኽ ኹኔታ ከቀጠለ የሕዝባችን ህልውናና የትውልዱም የወደፊት ዕድል አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል፡፡
  2. ባሳለፍናቸው ሳምንታት በተከሠተውኹኔታ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች በመሪር ሐዘንና በጸሎት እናስባቸዋለን፡፡ ስለዚኽ ኹላችሁም ልጆቻቸን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወንድ፣ ሴት፣ ወጣት፣ ሽማግሌ ሳትሉ ችግራችኹን ሰላማዊ በኾነ መንገድ ለሚመለከተው እንድታቀርቡ፣ መንግሥትም የሕዝቡን ችግርና ሰላማዊ ጥያቄ በመገንዘብ መፍትሔ በመስጠትና ሰላም ለማምጣት እያደረገ ያለውን የዕለት ከዕለት ጥረት እንዲቀጥልበት በቤተ ክርስቲያናችን ስም እናሳስባለን፡፡
  3. ሕዝባችንና ሀገራችን በርኀብ፣ በድኅነትና በበሽታ ቸነፈር በተቸገረበት ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት መሠረታዊ ወደኾነው ልማት የሰላምና የድርቅ ጉዳይ በማተኮር መልስ ሰጭ መኾን ይገባዋል ብለን በጽኑ እናምናለን፡፡
  4. ወገኖቻችን ሆይ፣ በአኹኑ ጊዜ የወቅቱ የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ(ብሎገሮችና የፌስቡክ) ተጠቃሚዎች የመኾን ምኞታቸው የላቀ ነው፡፡ ኾኖም መልካሙንና ለዕድገት የሚያግዛቸውን ዕውቀት እንጂ ኅብረተሰቡን የሚለያይና የሚያራርቅ መረጃ(ኢንፎርሜሽን) ዕለት ዕለት ብታስነብቡት ትርፉ መራራቅን እንጂ መቀራረብን፤ መለያየትን እንጂ መግባባትን አያመጣም፤ ከዚኽ አንጻር የእናንተም ጥረትና ድካም ከንቱ ኾኖ ይቀራል፡፡

በመኾኑም የተከበረ ዕውቀታችኹን፣ ሞያችኹን፤ ለሕዝባችን ፍቅርና አንድነት፤ ለሀገራችን ሰላምና ዕድገት እንድታውሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትጠይቃለች፡፡

የተወደዳችኹ ኢትዮጵያውያን፤

ተቻችሎና ተረዳድቶ የመኖር የተቀደሰ ነባር ባህላችንን የሚያጎድፍ ማናቸውንም አስተሳሰብና እንቅስቃሴ በአንድነት መቋቋም እንደሚገባ አበክረን እየገለጽን፣ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን በሙሉ በተለይም አገር ተረካቢ ትውልድ የኾናችኹ ወጣቶች ሁከትና ብጥብጥብን ከሚያስከትሉ መጥፎ ድርጊቶች እንድትቆጠቡ ለአገር ሰላምና ልማት ጠንክራችኹ እንድትቆሙ በልዑል እግዚአብሔር ስም አጥብቀን እያሳሰብን በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የሀብትና የንብረት ውድመት፣ በተለይም የሕዝብ መገልገያ የኾኑ የእምነት ተቋማት መቃጠል የተሰማንን ሐዘን እንገልጻለን፡፡

ይልቁንም ከኹሉም በላይ ኹሉን ማድረግ የሚችል እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ለሀገራችን ሕዝቦች ሰላሙን፣ ፍቅሩን፣ አንድነቱን ይስጥልን ዘንድ ትዳር፤ ድርቁን ረኀቡን አስታግሦ መጪው ጊዜ ዝናመ በረከቱን ይሰጠን ዘንድ በያዝነው በዐቢይ ጾም ሱባኤ ጸሎተ ምሕላ በመላ ሀገሪቱ ባሉት ገዳማትና አድባራት የገጠር አብያተ ክርስቲያናት እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ::
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ   

12 Comments on “ቅ/ሲኖዶስ: በመላው ገዳማት፣ አድባራትና የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ ዐወጀ::”

  1. መንግሥትም የሕዝቡን ችግርና ሰላማዊ ጥያቄ በመገንዘብ መፍትሔ በመስጠትና ሰላም ለማምጣት እያደረገ ያለውን የዕለት ከዕለት ጥረት እንዲቀጥልበት በቤተ ክርስቲያናችን ስም እናሳስባለን፡፡

  2. አልሰሜን ግባ በለው አሉ! እኛ ወያኔና ምናምንቴዎቹንም ከዛች የተቀደሰች ሀገር ድምጥማጣቸውን እንዲያጠፋልን ምህላ ከጀመርን ይኸው ሀያ አምስት አመት አለፈን።

  3. ayee abatochachin –

    weyanem yemelew ,,atanbibu atitsafu zim belachu tegezu new eko kk

    aynachn eyaye Hagerachn seneteq,, Hizb begef eyetegedele,,eyetasere,,eyetegerefe,,

    ketowinim Hagerachi newech Hailoch eji setgeba,,ketiwlid Hagerachin
    senefanaqel zim enbel ?

    TINISH YE ABUNE PETROSIN YAHIL BAYFETRIBACHU

    BAYHON ZEM BITLUN AYSHALIM ????

    EYETASERK EYEMOTK TEGEZA;; HAGERKIN ASALFEH SET NEW YEMITLUN ???

    YEHUN MIHILAW TIRU NEW KE AMLAK ERDATA ALENA INTSLIYANEN !

  4. እግዚኦ ማሃረነ ክርስቶስ ! ! ! የአቡነ ጴጥሮስን መቅደስ ባንዳ ሲያረክሰው ! ! !አበስኩ ገበርኩ ነው።አልሞትኩም ብየ አልዋዝሽም ! ! ! አባይ ጽሃየ ነብስህን አይማረው ! ! ! ልክ እናስገባዋለን ስትል ቆይተህ አሁን ደግሞ በአቶ ማቲያስ ይኸንን አሳወጅክ ! ! !

  5. የወያኔ ካባ ለባሽ ካድሬዎች ናቸው እንዴ ምህላውን የሚመሩት? እንዲህ ከሆነ ምህላው ራስቸውን ነው ጠራርጎ የሚያስወጣልን። ይቀጥሉበት ተዋቸው።

  6. አቤቱእውነቱና ውሽቱን አንተ ታውቃለህ።የተዘረፈውን ንብረት ሳይወስድ አንተ በሰማይ ያለህ ፍረድ ፍረድ እባክህን ።

  7. TOO LATE!!!
    666 supporter= Tehadiso + Menafek

    Everybody pray for your self no one is there fir u after His holly Abune Petros, Abune Tekehimnot, Abune Gorgorios. Ask your self that if u are in a bad situation in Libiya fellow Ethiopian scrifice for the truth. But, are u ready for that? You can see in a mirror your self how you are a voletile generation to speak the truth. Anyway to get back that heary cray and pray to your almighty God!

  8. ene betam betam ferahu

    be Ethiopia inba ena Dem eyefesese new !!! Gobez re tenesu Ethiopian enadin !!!

    Amara ena Oromo lelam hizbu tekefaflo weyanen indet masweged yechalal ?

    ERE TEWU AND INEHUN !!!!!

  9. which one is holly synods? don’t tell me the so called promoted by weyanes. I don’t believe he said this he steels and as if he is innocent he ordered people to pray. the best thing to do is to pray for weyanes to die one by one. that is my pray every day.

  10. በጣም የሚያሳስን ኦጅግም የሚያነስደነግጥ ዜና ነው፡፡እውነት በተቀደሰው ስፍራ ቅዱሳን የተሰኙ አባቶች ያሉት ሳይሆን የወያኔ መንግሣት ወይንም አባይ ፀሀይ ሲኖዶሱ ውስጥ ሹጉጡን ደግኖ በሉ የተባሉትን ያሉ እንጂ በእምነታቸው ጽናት በፀሎታቸው ብዛት አገራችንን ይታገዳሉ ብለን ጠዋትና ማታ በፊታቸው ወደቀን እግራቸውን ስመን በረከታቸውን የምንሻ ወገኖች ይህን ሰተሰማ ወገን ምን ያህል አዘንክ?እንግዲህ ተሰፋን ቁረጥ ለእምነቱ የቆመ ሳይሆን ለሹመቱ የቆመ መንፈሳዊ አባት የለህም የለሽም፡፡ምን አለ አንገታቸውን ለሰይፍ ከሰጡ ሳድቅ ወገኖች ቢማሩ፡፡መቼም ታሪክ ነውና ተመዝግቦ ይቀመጥ፡ሆኖም ነነጻነትህን በራስህ ሙሴን እያሰብክ ለድል ለበለጥ መነስዋእትነት እንዘጋጅ፡፡ነነጻቈነታችን የምናመጣው ራሳችን ከአምላካችን እግዚአብሔር ርዳታና ሀይል ብቻ ነው፡፡ተመልከቱ በርትታችሁ ተገዙ የሚል አባት ቀጣዪ አውግዘናል እንደሚሉን እናስብ፡፡ ደድል ፍትህና ነፃነት ደድህነት ላጠቃው ለኢትዮጽያ ህዝብ!!!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*