በኦሮሚያ የተለያዩ አከባቢዎች ተቃውሞ ቀጥሎ ውሏል::አዳዲስ ተቃውሞዎች በመጭው ሳምንት ይቀጥላሉ::

Minilik Salsawi's photo.

በኦሮሚያ የተለያዩ አከባቢዎች ተቃውሞ ቀጥሎ ውሏል::አዳዲስ ተቃውሞዎች በመጭው ሳምንት ይቀጥላሉ::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኢትዮጵያ የኦሮሚያ የተለያዩ አከባቢዎች ተቃውሞ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በምጥራብ አርሲ አሳሳ በምስራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ዶጉ ወረዳዎች በወለጋ በባሌ እንዲሁም በሸዋ ክፍለሃገሮች ተቃውሞ እና የመንገድ መዝጋቱ ተቃውሞዎች እንደቀሉ ይገኛሉ::በመጭው ሳምንት በተሻለ መልኩ አዳዲስ ጥያቄዎችን ያካተቱ የተቃውሞ ስልቶች እንደሚኖሩ ይጠበቃል:: ከፍተኛ ሃይል የሆነ የፌዴራል ፖሊስ እና የአግኣዚ መከላከያ ጦር በሻሸመኔ አቋርጦ ወደ ባሌ እየሄደ ይገኛል::

በምስራቅ ሃረርጌ የኦሕዴድ ጽ/ቤትን የተቆጣጠረው ሕዝብ በፌዴራል መንግስቱ ባንድራና በኦሕዴድ ባንድራ ምትክ የኦነግ ባንድራን ሰቅሏል::በዚሁ አከባቢ ሁለት ሰዎች የቆሰሉ መሆናቸው ታውቋል::በኦሮሚያ ክልል ለሚጌዙ ሰዎች ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሲሆን በመጭው ሳምንት ከፍተኛ ተቃውሞ ይስተናገዳል ተብሎ ይጠበቃል::ወደ አምቦ እና ጉደር የሚያስገቡ መንገዶች ዙሪያቸው መዘጋቱ ታውቋል::በአምቦ የጅምላ አፈሳ እየተካሄደ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል:: የጅማ እና ነቀምት ከተሞችን የሚያገናኘው መንገድ አርጆ ከተማ ላይ ተዘግቷል::በነጆ ከትላንትና ጀምሮ ትምህርት የተቋረጠ ሲሆን የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ በርካታ ዜጎች ለእስር ተዳርገዋል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬