ኃይሌ ምን አገባው ! ( ሄኖክ የሺጥላ )
ኃይሌ ምን አገባው ! ( ሄኖክ የሺጥላ )
ኃይሌ ወንድማችን ፣ ቆጣቢው ኃይሌ ፣አባ ሃናው ኃይሌ ፣ ባለፎቁ ኃይሌ ፣ ባለ ሲኒማ ቤቱ ኃይሌ ፣ የኦሎምፒክን ሜዳይ ደግሞ ደጋግሞ ያጠለቀው ትልቁ ሰው ኃይሌ ተሳሳተ ይላሉ ። አሁን ኃይሌ ምኑ ጋ ነው የተሳሳተው ? እኔ እስከሚገባኝ ኃይሌ የሚያውቀውን ነው ያወራው ፣ የገባውን ነው የተናገረው ! እኛ እኮ ኃይሌን ያወቅነው ኢትዮጵያውን ወክሎ ስለ ዲሞክራሲ ሲያወራ አይደለም ። እኛ ኃይልዬን የምናውቀው ሲሮጥ ነው ። አዎ ተዘጋጅ -ቷ ! ከዛ በቃ ሀይልዬ ፍልቅልቅ እያለ ሲሮጥ !
ኃይሌ ለኢትጵያ ሕዝብ ዲሞክራሲ እንደ ቅንጦት ነው ፣ መልካም አስተዳደር እንጂ ዲሞክራሲ አያስፈልጋትም ሲል ስህተቱ ምኑ ላይ ነው ? ተሳሳተ እንዴ ?እንደውም ኃይሌ ከተሳሳተ የተሳሳተው የኢትዮጵያ ሕዝብ መልካም አስተዳደር ችግር ሊኖርበት ስለሚችል ፣ የመልካም አስተዳደር ያስፈልገዋል ማለቱ ነው ። እኔን እስከሚገባኝ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም አያስፈልገውም ! ምንም !
ቆይ መልካም አስተዳደር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ይሰራለታል ? ምን ሊያደርገው ? የት ሊያስቀምጠው ? አሁን ማን ይሙት ለአንድ ገበሬ ዲሞክራሲ ብትሰጠው ምን ያደርግበታል ? አያርስበት !? አይጎለጉልበት !? አይዘራበት !? ምን በወጣው ። እዛው ዲሞክራሲውንም እንደ መሬቱ እርስ በእርሳቸው ይከፋፈሉት ! ኃይሌ ልክ ነው ባካችሁ !
አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ የነጻነት ጥያቄ መጠየቁ አግባብ ነው ነው የምትሉት ? ነጻነት ምን ይሰራለታል ? ግዛ ብትሉት ዋጋውንስ ይችለዋል ወይ ? ነጻነት እኮ ብዙ ያስከፍላል ? ዲሞክራሲ እኮ ” እንደ ሾላ ፍሬ በድንጋይ ተመቶ የሚለቀም ነገር አይደለም !” ። እንደውም ሳስበው የኛ ሕዝብ ችግር ስለማያውቀው ነጻነት ማውራቱ ላይ ይመስለኛል ። ይሄ ሕዝብ ነጻ ሆኖ ያውቃል እንዴ ? ታዲያ ያለመደበትን ነጻነት ማንን ለመመስል ነው ” ነጻነት -ናጽነት – ፕሊሱማ –” እና ወዘተ እያልን የምንደሰኩረው ። «ከየት አባቱ ያመጣውን ነጻነት !» እንደውም የዚህ ሕዝብ ችግር ቂጥኝ ነው ! የዚህ ሕዝብ ችግር የዲሞክራሲ እጦት ሳይሆን ፣ ያልተመጣጠነ «ወሲብ» ችግር ነው !
ይሄ ሕዝብ እኮ ዓመት ሙሉ እህል ሳይበላ ፣ ለአምት-በዓል በግ የሚያርድ ሕዝብ ነው ። ታዲያ የዚህ ሕዝብ ችግር ከዲሞክራሲ እጦት ጋ ምን አገናኘው ? የዚህ ህዝብ ችግር የመስ’እዋት ችግር ነው። ለምሳሌ የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት በያ ሰሞን ሲሰረዝ ፣ የአስቴርን የሙዚቃ ኮንሰርት ተቀላቅሎ ይህ ብርቅ ሕዝብ ሲጨፍር እንዳደረ ሰምቻለሁ። ምን ማለት እንደሆነ ይተርጎም ? እሺ ይህንን ስንተረጉመው ምን ማለት ነው የ- አንድነት ፓርቲ በምንወደው መንግስታችን በጉልበት ሲፈርስ ፣ ሄዶ ሰማያውን መቀላቀል ማለት ነው ። ታዲያ ለዚህ ሕዝብ ዲሞክራሲ ያስፈልገዋል ? በምድር ላይ ከዚህ ሕዝብ በላይ ያለ ዲሞክራሲ– ዲሞክራሲን የተረዳ ይኖራል ?
ሀይሌ እውነቱን ነው ፣ ለዚህ ሕዝብ ዲሞክራሲ ሳይሆን ካልሲ ነው የሚያስፈልገው ! ለዚህ ሕዝብ ነጻነት ሳይሆን ፣ ፓንት ነው የሚያስፈልገው ። የዚህ ሕዝብ ችግር የመልካም አስተዳደር ችግር ሳይሆን ፣ የመልካም ምድራዊ አቀማመጥን በትክክል ያለመረዳት ችግር ነው ። ምን ማለት ነው ? ይሄ ሕዝብ ሃገሩ ራሷ የቱ ጋ እንዳለች እንኳ በቅጡ አያውቅም! ለዚህም ነው በአራቱም አቅጣጫ ሃገሩን ለመፈለግ ካገሩ የሚወጣው ! የዚህ ሕዝብ ችግር የመንግስት ባለ ስልጣናት የሚያደርሱበት በደል አይደለም ! የዚህ ሕዝብ ችግር ያንን በደል ችሎ ( ዋጥ -ሥልቅት አድርጎ ) መኖር መቻሉ ላይ ነው ። ታዲያ ህዝቡ ረሃቡ ከተመቸው ፣ ድንቁርናው ከደላው ፣ ስደቱ ከከየፈው ፣ ኃይሌ ምን አገባው ! ደሞ ኃይሌን እናውቀዋለን እንጂ እሱ አያውቀንም ! ቢያውቀን ኖሮ እንዲህ አይለንም ! እመኑኝ ኃይሌ አያውቀንም !

Binagrim bayinagerim yemayamribet sew-Haile
Haile esti zeeeeeeeeeeeeeeeeeeem bel!ufffffffff Egir chenkelat new ende ebakekkkkkk wel engede!
Haile lehodu yadere nw.
Yihe foto ye sew new ye zinjero new?
god bless haile
የዓለም ትልቁ መልከ ጦጣና ልጋጋም፤ ደንቆሮ፤ሐይሌ!!!
Hailen nege bizu neger sileminiteyikew zimmmmmm new.
Hailen nege bizu neger sileminiteyikew zimmmmmm new.
ይች አገር ለጉድ የተፈጠረች ናት። ከናቲራውን ከራሱ ላይ አውልቆ ለዚያ draculla ስጠ ከተባለ በኋላ በትልቁ ትልቅ X አስቀምጨበት የተውሁትን መሃይም ሚዲያ ላይ አምጥታችሁ ሞላችሁብኝ።እሩጦ እሩጦ ያጠራቀመውን ሃብት በምን እንዲከላከለው ትጠብቃላችሁ? እባካችሁ ተውት።
ወንድማችን ኃይሌ ገ/ስላሴ ላይ ሰሞኑን ለቢቢሲ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ ብዙ በትር እየተወረወረበት ነው። ይህ የሆነውም በሁለት ምክንያት ነው። አንደኛው ኃይሌ ማለት የፈለገውን በደንብ ባልተረዱ ወይም ለመረዳት ባልፈለጉ ወይንም ኃይሌን ለመምታት ጊዜ ሲጠብቁ በነበሩና አሁን ነው መምታት ባሉ ፀጉር ሰንጣቂዎች ምክንያት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ኃይሌ ማለት የፈለገውን ከግንዛቤ እጥረት ወይንም ከአገላለጽ ችግር በደንብ ስላላስቀመጠው ነው። ኃይሌ ያለውን በቅንነት ካየነው የምትበላው የላት የምትከናነበው አማራት ማለት ነው የፈለገው። እንዴት ዲሞክራሲ አያስፈልግም ትላለህ ብሎ ሲጠይቀው ይቅርታ ያንን ማለቴ አይደለም ቅድሚያ ለመልካም አስተዳደር እንስጥ ማለቴ ነው ብሎ ማስተካከሉን ለምን እንስታለን?
ወንድማችን ኃይሌ የሳተው ግን መልካም አስተዳደር ያለ ዲሞክራሲ ሊመጣ ይችላል አይችልም የሚለውን መመርመር ነው። አፍሪካ በአሁኑ ጊዜ ወደ ልማት የሚውስዳት ጠንካራ መሪዎች ያስፈልጓታል የሚሉ ግን ብዙ ናቸው። ስለዚህ ኃይሌ ለኢትዮጵያ በጎ ነገር እንጂ ክፉ እንደማያስብ እያወቃችሁ ብሄራዊ እስቴቶቻችን በማውደም የምትራኩ አውዳሚዎች ኃይሌን ለቀቅ አድርጉት። ወንድማችን ኃይሌ ሌላ ጊዜ ስትናገር ትንሽ እያገናዘብክ ሀሳብክን ግለጽ ምክያቱም ማንንም ለመምታት ወደ ኋላ የማይል ተንኮለኛ የሞላበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው።
yehe demo kersam
hodu lemola kesu kemola min chegerew esu ?
Mehayim
Mortu ^!
Lemendin neaw
Ginbotoch hulgize
sedebachew hodam ,
lehodu belo yemesaselu nachew.
Lehodachew belew ye
Isayasn iger
Ymiyatbu
Ene yemlew hailen Beastesasebu endenegnawem sew leme atkotrutem?
ማንም ተነሥቶ መንግሥት ልሁን የሚልባት ሀገር ሆነች የቀዳማዊ ኅ.ስላሤን እርግማን ትውልዱ ካላወረደ እንዲሁ በወያኔ መክኖ መቅረቱ ነው
እሱ አያውቀንም የሚለው ሀሳብ ሊያስማማን ይችላል ግን ይህን ሰው የትግላችን ችቦ ለማድረግ በጣም ወሳኝ ልንለው እንችላለን ግን ይህን አካሄድ የአማራ ልሂቃን አይዋጥላቸውም ትግሉ ብሄር ተኮር እንዲሆን አይፈለግም ለዚህም ማስረጃ እስካሁን ያልበረደውን ትኩሳት መዳሰስ እንችላለን ይህን ችቦ አልቀባበል ያሉ ልሂቃን በጋራ ማብረት ካቃታቸው ያው ጎጆው ላይ መወርወሩ አይቀሬ ነው ይህንም ማሳቸሁን ማን አቃጠለው? ይህን ጡረተኛ ሯጭ ትልቅ ብሄራዊ ንቅናቄን ሊያመጣ ስላሚችል ወገቡን ሉጓም ከተን ብናሯሩጠው መልካም ይመስለኛል።
********************************
Min yimslal bakachihu?? Jinjero
Diros esu Egir enji Ras endelelewu atwukum ende ?
Good clarification ,THANK’S
Athelet Haile Gebre Selasse ”Think twice before you speak once”…
Its a nice analysis I like your
being who you are .
HAILE has a reason to support WOYANE mafia group, he is business partner with AZEB GOLA, own RESORT IN HAWASSA, ZEWAY, LUXURY VILLAGE (VILLAS, APRTMENT) IN SULULTA, & more.
its sad people are being killed cause they ask their basic rights, and HAILE is spiting on Ethiopian people with an ugly word that come out of his big mouth.
ተውኝ ወንድሞች ብአዴን የሚባል ድርጅት የለም!
ቢኖርማ ራሳደጄን ተራራ ወደትግራይ ክልል ሲከለል ለምን የሚል ጥያቄ ያስነሳና መፍትሄ ይፈልግ ነበር
አማራ አከርካሪው ተመትቶል ኦርቶደክስም፣እስልምናንም ለመጨረሻ ጊዜ ድባቅ በወያኔ ሃይል ተመትቶል
የብአድን አባላት የሚባሉት ሃይሎች ሆዳሞችና ከርስ አደሮች እና ከዚያ ውጭ ያለ ካለ አርካሪውን በተደጋጋሚ የተመታበት መሆኑን ይታወቃል፡፡
ይች ሃገር ከዘመን ዘመን እየፈረሰች አንድነቶ፣ግዛቶ፣እየላላ፣ዝህቦም በርሃብ እየሞተ ስደት እየነጎደ ነው! ምን ይሻላል?
ሰ.አ
haile gebresilasse is always “foot”.he runs;thinks;speaks…by his foot¡.trojan horse!
ጉድ ነው ወንድሞች! ሃይሌ ገ/ስላሴ አበደ መሰለኝ? ምን ነካው? ከማንስ ጋር ዋለ ይህ ሰው ሃብት አሳበደው እንደ መቼም ከዘመኑ ሰዎች ጋር አብሮ መዶለት ጀመረ ወይም የማሰቢያው ሶፍትዎር ቀየሩለት
ለአፍሪካ ድሞክራሲ አያስፈልግም ዋይ !ተው ሃይሌ እንደሰው አስብ አማካሪህንም ምን እየሰራሁ ነው በለው?
አላህ እንደሰው ያድርግህ ከቻልክ ማሰብ ካልቻልክ ተዎው
ሰ.አ
well said sir, the writers themselves have lacked good judgment
I support Haile