በኢትዮጵያ ፍትሕ፣ እኩልነትና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ሲታገል የኖረው አቶ በላይ ወንዳፍራሽ (እንደዜጋ/ሰላምሁን PalTalk name)በጀርመን ሃገር አረፈ።

IN MEMORY of Mr. Belay Wendafrash From Voice of Ethiopian youth

በጀርመን ሃገር እና በመላው አውሮፓ ኢትዮጵያውያንን በማሰባሰብ ለታፈኑትና ድምጽ አልባ ለሆኑት ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ሲሟገት የኖረው ወንድማችን አቶ በላይ ወንዳፍራሽ ቅዳሜ ኖቬምበር 28፣ በፍራንክፈርት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ጸሎተ ፍትሐት ከተደረገለት በኋላ አስክሬኑ ወደ ኢትዮጵያ ተሸኝቷል።

አቶ በላይ ወንዳፍራሽ ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ በነበረበት ወቅት በወያኔ ደህንነቶች በተቀነባበረ ሴራ የመግደል ሙከራ ተደርጎበት በሦስት ጥይቶች ተመቶ የተረፈ ጀግና ወንድማችን ነበር።በዕለቱ ማህበረ ካህናቱም ሆኑ በወቅቱ የተገኙ ወዳጆቹና አክባሪዎቹ ፣ አቶ በላይ ወንዳፍራሽ ዘር፣ጎሣ ሳይለይ ሁሉንም ሲረዳ የኖረና የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ አንግቦ እስከ መጨረሻው ነጻነትን የሰበከ ሐዋሪያችን ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡እኛም እግዚአብሄር የወንድማችንን ነብስ በገነት ያኖርልን ዘንድ እንመኛለን።

Voice of Ethiopia Youth

IN MEMORY of Mr. Belay Wendafrash From Voice of Ethiopian youth
ለአቶ በላይ ወንዳፍራሽ መታሠቢያ ከኢትዮጲያ ወጣቶች ድምጽ
[youtube http://www.youtube.com/watch?v=NffGwLHu5Eo]