የድርቁ ተጠቂዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው
የድርቅ ሰለባ ህዝባችን መንግስት ይፋ ካደረገው ኣንድ ሚልዮን ተጠቂ ህዝብ በሁለት እጥፍ የበለጠ ነው።
ሰሞኑን ኣቶ ኣባይ ወልዱ በምስራቃዊ ዞን 2 ወረዳዎች( ኣፅቢወንበርታና ክልተኣውላዕሎ)፣ ደቡባዊ ዞን( ራያ ኣላማጣና ራያ ዓዘቦ) ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ህዝቡ በግልፅ የድርቁ ሁኔታና ኣደገኝነቱ ነግሯቸዋል።
በሁሉም ወረዳዎች ከተሰጣቸው ኣስተያየት ” የመጣው የእርዳታ ኮታ እጅጉን ኣነስተኛ ነው። ለማን ሰጥተን ለማን እንከልክል፣ “እኔ እብሳለው እያላቹ ውሰዱ” የሚለው ውሳኔያቹ በረሃብላይ ጥላቻና ቂምበቁል በማበጀት የማይጠፋ ጠባሳ ትቶ እንዲያልፍ እያደረጋቹ ነው። ከብቶችና ሰው የሚጠጡት ውሃ የለም፣ ሰው እየተሰደደ ነው፣ ልጆች ትምህርታቸው እያቋ ረጡ ነው( ኣባይ ወልዱ ስለ ትምህርት መቋረጥ የተናገሩት ” ትምህርት ያቋሩጠ ተማሪ ካለን ድርቁ ኣሸነፈን ማለት ነውና እንዲመለሱ ኣድርጉ ብለዋል)፣ትንሽ ተገትቶ የነበረው የወጣቶች ስደት እንዳዲስ መጀመሩና ፈርሶ እየሄደ መሆኑ፣ የሰው ሂወት በረሃብ እያለፈ መሆኑ ጎብኝዎች በኣፅቢወንበርታ በረሃብ የመቱት ወይዘሮ ቤት ጎብኝተው ኣረጋግጠው መጥተዋል።
በሁሉም የተጎበኙ ወረዳዎች የመጣው የእርዳታ እህል እጅግ ትንሽ በመሆኑ ባሽቸኳይ እንዲጨመርና የሂወት ኣድን ስራ እንዲከወን ህዝቡ ጠይቋል። የእርዳታው ኮታ ለኣንድ ሚልዮን ህዝብ ተብሎ የመጣ ነበር።
ኣቶ ኣባይ የእርዳታ ኮታው ያንሳል የማል ሃሳባቹ ተቀብለናል፣ መንግስት ትላልቅ ፕሮጀክቶች ኣጥፎም ቢሆን ሂወት ለማዳን ይሞክራል ብሏል።
ጎብኝዎቹ መሬት ላይ ባለ ድርቅ ከጠበቁት በላይ እንደሆነና ለከፋ ኣደጋ እንደሚያጋልጥ ተገንዝበዋል።
በራያ ዓዘቦ ኣስተያየት የሰጡት ኣንዲት እናት በሂወቴ እንደዚህ ዓይነት ድርቅ ኣጋጥሞኝ ኣያውቅም። የ77 ድርቅ እንኳን የዚህን ያህል ኣልነበረም። ብያንስ ከብቶቻችን የሚመገቡበት በለስ( ቁልቋል) ነበረባቸው። ኣሁን በለስም የለም ከብቶቻችንና ሰዋችን የምናበላው የለንም…” ብለዋል።
የድርቁ ስፋት በሁለት ሳምት ብቻ ከ190 ወደ 230 በላይ ቀበሌዎች ኣስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው እየተገለፀ ነው። የራያ ዓዘቦ ወረዳ ድርቅ ያጠቃቸው በብለው ተጠንተው የነበሩት18 ቀበሌዎች ወደ 21ከፍ ብለዋል። ወረዳዋ ካሏት ከ23 ቀበሌዎች ነው።
መንግስት 25 ዓመት ሙሉ ድርቅ መከላከል የሚችል ኢኮኖሚ ካለመገንባቱ በላይ ድርቁ ለመደበቅና ለማቃለል እያደረገው ያለው ጥረት ይበልጥ ኣሳፋሪ ያደርገዋል።
ኣሁን በትንሹ ከሁለት ሚልዮን በላይ ህዝብ ኣስቸኳይ የእህል እርዳታ ያስፈልገዋል።
እያንዳንዳችን ለዚህ ህዝብ ሂወቱ ለማትረፍ ኣንድ ነገር ማድረግ ኣለብን። እርዳታው ለማስተባበር መንግስት ኣቅም የሚያንሰው ከሆነ ዓረና ሃላፊነቱ ለመውሰድ ይገደዳል።
የኣማራ ክልል በድርቅ የተጠቁ ዞኖች እንደ ዋግ ኽምራ ዞን፣ የበለሳ፣ የራያ ቆቦ ዞኖችም ተመሳሳይ ኣደጋ ውስጥ ይገኛሉ። ህዝባቸው እንዳይሰደድ መሬትህ ትነጠቃለህ ተብሎ ለኣደጋ ተጋልጦ ይገኛል። መሬት የሌላቸው ወገኖች መቐለ ከተማ በብዛት መጥተዋል።
ዓፋር ክልል ኣስቀድሞ የፌደራል መንግስት ድጋፍ እየተደረገለት ይገኛል። የኦሮምያና ሶሜሌ ክልሎችም የድርቁ ሁኔታ እየተባባሰ እንዳለ እየተገለፀ ነው።
ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች፣ ሙሁራን፣ የሃይሜኖት ተቋማት፣ የልማት ማህበራት ኢህኣዴግ በድርቁ ለተጠቁ ወገኖች ባስተማማኝ ሁኔታ ሊደርስላቸው ኣቅምና ወኔ ያንሶዋልና እጃቹ ዘርጉ።
ድርቁ በፈጠረው ረሃብ ሂወት ኣልጠፋም እያላቹ ለምታመካኙ ወገኖች ይሄው ምሳሌ የሚሆን ድርቁ የፈጠረው ረሃብ ሰለባ ኣግኝታቹሃልና እጆቻቹ ዘርጉ።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
IT IS SO………!
Amdom Gebreslasie



