በኢትዮጵያ ከ7.5 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በከፍተኛ የረሃብ አደጋ እየተጎዳ ነው:: ወደ 15 ሚሊዮን ያድጋል ተብሎ ተፈርቷል::

Minilik Salsawi ካለፈው ነሃሴ ወር 2007 ጀምሮ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት በትግራይ አፋር አማራ ኦሮሚያ እና ደቡብ ክልል በከፍተኛ ደረጃ በተከሰተው ድርቅ ቀደም ሲል ቁጥሩ ከተጠቀሰው 2.5 ሚሊዮን በረሃብ የተጎዳ ሕዝብ ቁጥሩ አድጎ 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የነበረ ሲሆን አሁንም የወያኔው መንግስት የሕዝብን ሃብት አንቆ ወገኖቻችንን ለመርዳት ዝግጁ ባለመሆኑና የለጋሽ አገሮች እርዳታ ለማግኘት የተለመነው ባለመሳካቱ በረሃብ የተጎዳው ሕዝብ ቁጥሩ እየጨመረ ሲገኝ ባሁን ወቅት ሰባት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሕዝብ በከፍተኛ የረሃብ እደጋ እየተጎዳ መሆኑ ታውቋል::

ይህ የዝናብ እጥረት እና የኤልኒኞ የአየር ጸባይ የፈጠረው ድርቅ ያስከተለው ከፍተኛ የረሃብ አደጋ በመስፋፋት ላይ ቢሆንም በተለያየ ጊዜ የወያኔ ባለስልጣናት ረሃቡን ለመሸፋፈን እና ለመደበቅ ለማደናበር ቢሞክሩም ረሃቡ አግጥጦ በመውጣት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የምግብ እህር ዕርዳታ እደሚያስፈልጋቸው የእርዳታ ድርጅት ባለስልጣኖች እየተናገሩ ይገኛሉ::የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በነሃሴ መጨረሻ ላይ ባወጣው ዘገባ 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል ሲል ባለፈው አንድ ወር ግን ድርጅቱ ካወጣው ዘገባ በእጥፉ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ውስጥ እየዋኘ እንደሚገኝ ተገልጿል::በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ ከ15 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ይጎዳል ተብሎ ሲጠበቅ ይህ ደግሞ በሶሪያ በጦርነት ከሚጎዳው ሕዝብ በላይ መሆኑን ዘገባዎች ይጠቁማሉ::ለዚሁም የተባበሩት መንግስታት አንድ ተግባራዊ እርምጃ ካልተወሰደ አደጋው የከፋ እንደሚሆን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

4 Comments on “በኢትዮጵያ ከ7.5 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በከፍተኛ የረሃብ አደጋ እየተጎዳ ነው:: ወደ 15 ሚሊዮን ያድጋል ተብሎ ተፈርቷል::”

  1. ለወገን ደራሽ ወገን ነው ወይሥ ባንዳ?

    አንድ ብር ላንድ ወገን በሚል ወ/ሮ ሰሎሜ የተመዘበረው አይነት ድራማ እውን ሊደገም ይሆን? ለወገን ደራሽ ወገን እንጂ ዘራፊው ወያኔ አይደለም።

  2. እሥከመቼ ነው ወገን ለልመና ድርድር እየቀረበ የምንኖረው በምግብ

    ራሣችንን ችለናል ብለው እንዳህያ ሢያናፋ የነበሩ ጉጅሌዎች አሁን ነው

    እንደጅብ ጉድጓድ መቆፈርና መደበቅ የመረጡት ለምንሥ የክምችት እህል

    በፖርላማ ፀድቆ እንዲሸጥ ተደረገ የዶላር ጥማት በወገን ረሀብ መርካት

    እጅጉን ኢሠብአዊ ድርጊት ነው ከተጠያቂነት አያመልጡም ቀድሞ ጢሻ

    የገባነው መሬት ላራሹ እንዲሁም ገበሬው የዘመናዊ እርሻ ባለቤት ሆኖ

    ራሡን ከድህነት አረንቋ ለማውጣት ወያኔ ይህን ለውጥ አመጣ ብሎ ከበሮ

    በመደለቅ የሚሊኒየም ጎል ማሣካት ልባጩ የቀብር ልፈፋ ሆኖ ተገኝቷል

    ታድያ ይህ ጢሻ የከተታቸው ተጋድሎ እውነት ድርቅን ረሀብን ለማጥፋት

    ነው?ወይሥ ኢትዬጵያን ለመበታተን ትግራይን ነፃ ማውጣት የቱ ጋር እንዳሉ

    ፍረዱት ሟቹ መሪ ውሀ ማቆር ብሎ ከፍተኛ ወገን በወባ እንዳለቀ ድብቅ

    አጀንዳቸው ነበር ይህ አልነበረም ገበሬውን 1ለ5 በማደራጀት የወገንን

    ከረሀብ ማላቀቅ ሣይሆን የግንዛቤውን ድክመት ተጠቅመው የኮሮጆ

    ሥልብናን በማግኘት የወያኔን ግዛት ማሥቀጠል ከዚህ በዘለለ ሀቅ ሊሠወር

    አይችልም ከእሥታክሥቲኩ ዳታ ድንጋጤ የህዝብ ቁጥር ማሻቀብ አንፃር

    የወያኔ ጫንቃ ሊሸከመው በማይችለው የኢኮኖሚ ውዥቀት የወገንን

    እንደቅጠል መርገፍ እንደጥሩ አጋጣሚ ይወሥዱታል ይህን ሥናይ

    ለወገናችን ዘለቄታዊ መፍትሄ ለማምጣት የሚታገለው የሀገር ወዳድ

    ንቅናቄዎች በሙሉ ወደ አንድ አላማ ተሠባሥቦ ይህን ለወገን ደንታ

    የሌለውን ወንበዴ ድርጅት ማሥወገድ ይኖርብናል።

  3. እኔ እኮ ግርም የሚለኝ በህወሀት መስመር ገበሬው እጥፍ ማምረት ጀመረ እያሉ የኢትዮጵያን ህዘብ ቀን ከለሊት አደነዘዙት ከፈረንጅ ቅጥረኛ በሙስና ሽልማት እየተቀበሉ በምግብ እህል እራሳችንን ስለቻልን ነው በማለትም እዮኝ እዮኝ አሉ ዛሬ ግን የሰው ልጅ እንደ ቅጠል እየረገፈ አነሱ ዴንታም የላቸው አይሰሙም ጆሮአቸውን በሌብነት ዶላር ደፍነውታል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*