ለሙሽሮች በተዘጋጀ ድግስ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ጉዳት ደረሰ

ኮተቤ አካባቢ ለሙሽሮች በተዘጋጀ የመልስ ድግስ ላይ በኃይልና በጉልበት “ድንኳን ሰብረው” በገቡ ጎረምሶች በርካታ ተሽከርካሪዎች መሰባበራቸውንና በተጋባዥ እንግዶችም ላይ ጉዳት መድረሱን የሙሽሮቹ የቅርብ ዘመዶች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡