ረብሻ አስነስተዋል በተባሉ የጐንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ቅጣት ተላለፈ

ከአንድ ወር በፊት በጐንደር ዩኒቨርሲቲ ተከስቶ በነበረው ወረርሽኝ በሽታ መነሻ፣ ረብሻ በማስነሳት በዩኒቨርሲቲው ንብረት ላይ ውድመት አድርሰዋል በተባሉ 30 ተማሪዎች ላይ ዩኒቨርሲቲው ቅጣት አስተላለፈ፡፡