የሽብር ተከሳሾች ‹‹አኬልዳማ›› ክብራችንንና የፍርድ ቤቱን ክብር ነክቷል አሉ

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው እነ አንዱዓለም አራጌ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ‹‹አኬልዳማ›› በሚል ያዘጋጀው ፕሮግራም የእኛንና የፍርድ ቤቱን ክብር ነክቷል፣ ስማችንንም አጉድፏል፤›› በማለት ኅዳር 20 ቀን 2004 ዓ.ም. ለፍርድ ቤቱ አመለከቱ፡፡