አጠቃላይ ምርጫ በዴሞክራሲያዊት ኮንጎ

በዴሞክራሲያዊት ኮንጎ ሬፑብሊክ በዛሬው ዕለት ፣ እአአ ኅዳር 28፣ 2011ዓም አጠቃላይ ምርጫ እየተካሄደ ነው። ለፕሬዚደንታዊው ምርጫ አስራ አንድ ዕጩዎች፣ ካለፉት አስር ዓመታት ወዲህ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ያሉት የአርባ ዓመቱ ፕሬዚደንት ጆሴፍ ካቢላ ጭምር ለውድድር ቀርበዋል።