የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ትምህርት ቤቱንና የትምህርት ቢሮውን አወዛገበ

የምሥራቅ ድል አንደኛ ደረጃ የሕዝብ ትምህርት ቤት መንግሥት ከሕግ ውጭ ጣልቃ በመግባት አመራሮችን እየሾመ ነው በሚል ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በመወዛገብ ላይ ነው፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት በበኩሉ ትምህርት ቤቱ አመራሮችን በሕጉ መሠረት እኛ እንሾማለን ካለ መንግሥት ድጋፉን ያቋርጣል አለ፡፡