መንግሥት 132 ሺሕ አባወራዎችን በመንደር ሊያሰባስብ ነው

ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች የሚገኙ 132 ሺሕ አባወራዎች በያዝነው ዓመት በመንደር ተሰባስበው የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ አገልግሎትና የመሠረተ ልማት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡