የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር አሥር ሚሊዮን ብር ዕግድ ፀና

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ሕግ ከሚፈቅደው ውጪ የሰበሰበው አሥር ሚሊዮን ብር ከባንክ እንዳይንቀሳቀስ የሰጠውን ውሳኔ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 11ኛ ፍትሐ ብሔር ልደታ ምድብ ችሎት አፀናው፡፡