የዋጋ ግሽበት የኢንሹራንስ የአረቦን ዋጋን እያናረው ነው

ለተሽከርካሪዎቻቸው ኢንሹራንስ የገቡ አንዳንድ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለሚሰጡን ዋስትና እስከዛሬ ስንከፍል ከነበረው አረቦን በላይ እየተጠየቅን ነው ሲሉ፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ደግሞ ይህ የሚታወቅ አሠራር እንጂ በደንበኞች ላይ ዋጋ ለመጨመር አይደለም ብለዋል፡፡