በደቡብ ክልል 42 ኮሌጆች/ተቋማት ለመጪው ዓመት ምዝገባ እንዳያካሂዱ ታገዱ

– ተቋማቱ በዓመት በአማካይ 35 ሺሕ ተማሪዎችን ይመዘግቡ ነበር

(በምዕራፍ ብርሃኔ)

በደቡብ ክልል የሚገኙ 42 የግል ትምህርት ተቋማትና ኮሌጆች ከነቅርንጫፎቻቸው በድምሩ 73 ማሠልጠኛዎች፣ ለ2003 ዓ.ም. ምዝገባ እንዳያካሂዱ ታገዱ፡፡