ሲአይኤ ፤ መለስ ዛናዊ ፤ ኢትዮጵያ (ክፍሌ – 1)
በሉሉ ከበደ
ዘመኑ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1990 ሊይ ነበር ። አደርግ የአስተዳደርና የፖለቲካ ድህነት ምስጋና ይግባውና ሐገራችን ከገንጣይና አስገንጣይ ሀይልች ጋር ታደርግ የነበረው ትንንቅ በኛ ሽንፈት ወደማክተሙ ሲቃረብ ፤ ዋናው ምክንያት የወያኔና የሻእቢያ ጦር ከኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ጀግናና ሐያሌ ሆኖ ሳይሆን ፤ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት በገጠመው የአመራርና የአስተዳደር ቀውስ የውጊያ ሞራሉ ሊጠገን በማይችል መሌኩ ስለተጎዳና ውግያውን ስለተወው ፤ በሩ ሁለ ለጠላት ክፍት ሆኖ በመገኘቱ ነበር።