የታላቁ ቤተ መንግሥት ግምጃ ቤት ኃላፊ በ12 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተጠየቀ

በአራዳ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ቀበሌ 15/16 ክልል ልዩ ቦታው አራት ኪሎ ታላቁ ቤተ መንግሥት ውስጥ አንድ የግምጃ ቤት ኃላፊና አንድ ሾፌር በ12 እና በአምስት ዓመታት ፅኑ እስራት፣ በ20 ሺሕ ብርና በአምስት ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ዓቃቤ ሕግ ጠየቀ፡፡