“ሌባው” ዳኛ እና አሸባሪው አዋጅ – ሲሳይ አጌና

ግንቦት ሰባት፣ኦነግ እና ኦብነግ ከድንበር ዘለሎቹ አልቃይዳ እና አልሻባብ ጋር በአሸባሪነት በተፈረጁ በሳምንት ግዜ ውስጥ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና መምህርት ርዕዮት አለሙ ታሰሩ፤በአሸባሪነትም ተከሰሱ፤ወን ላቸውም በስልክ እና በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ከደረሰ ጉዳት ጋር መያያዙ 15 ዓመታት ወደሁዋላ ወሰደኝ፤ይህ ወቅት እኔ እስር ቤት የነበርኩበት፣የዛሬው የጋዜጠኞቹ ወንጃይ እና ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል በአቶ መለስ ዜናዊ ሌባ ዳኛ ተብሎ የተባረረበት፤ይህም ብቻ አይደለም ዛሬ በሽብር የተፈረ ው የስልክ ገመዶች መቁረጥም የተጧጧፈበት ግዜ ነበር።