ይድረስ ለአቶ ግራማ ካሣ – ታምራት ታረቀኝ
ከታምራት ታረቀኝ
አቶ ግራማ ካሣ ማንን እንደሚሞግቱ ለምንስ እንደሚሟገቱ የሚያውቁ አይመስልም። በሌሎች የሚሰጡ አስተያየቶችን በቅጡ አንብበው ጭብጡን ተረድተው ሊጽፉ ቀርቶ ከራሳቸው ሃሳብ ጋርም በወጥነት የሚዘልቁ ላለመሆናቸው አንድ ሁለት ጽሑፎቻቸውን ማየት ብቻ ይበቃል። በቀናት ልዩነት የሚጽፉት ቀርቶ በአንድ ቀን የሚጽፉዋቸው ሳይቀር እርስ በርስ የሚቃረኑ ለመሆናቸው ጽሑፎቻቸው ይመሰክራሉ።
ምርጫ ቦርድ የአንድነት ሊቀመንበር ኢ/ር ግዛቸው እንደሆኑ አድርጎ በድረ ገጹ አሰራጨ። የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ናትና ድርጊቱ የተፈጸመው በምርጫ ቦርድም ይሁን በእነ ኢ/ር ግዛቸው ሕጋዊ የሚሆንበት መሠረት የለውም ብዬ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ምዝገባ አዋጅና የአንድነትን መተዳደሪያ ደንብ ጠቅሼ ጻፍኩ። አቶ ግራማ የሰጡትና እየሰጡ ያለው አስተያየት ግን እኔ ካነሳሁት ጭብጥ ጋር የማይገናኝ ነው። የተቃውሞአቸው ምንክያት አልገባኝም። ነገረ ሥራቸው ሁሉ ”በምኒልክ ዘመን የደነቆረ ’ምኒልክ ይሙት!’ እንዳለ ይኖራል” ይሉ አይነት ነው። አቶ ግራማ የትናንት መነጽራቸውን አውልቀው በአዲስ መነጽር ጽሑፌን ቢያነቡትና በሚገባ ቢረዱት ስህተት የማይሰለቻቸው ቢሆንም የተሳሳተ ሃሳብ ከመሰንዘር ያድናቸው ነበር። … (… ሙሉውን ጽሑፍ በፒዲኤፍ ያንብቡ)