የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ሁለተኛ ቀን ባስደሳች ሁኔታ አለፈ

Ethiopia Zare (እሁድ ሰኔ 26 ቀን 2011 .. July 3 , 2011):- አርብ፡ ጁላይ 1 ቀን በዋሽንግተን ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ የተከፈተው የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ያዘጋጀው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አመታዊ ፌስቲቫል  በሁለተኛው ቀን በተሳካ ሁኔታ ቀጥሎ ውሏል። ዛሬ እሁድ ፍጻሜ ይሆናል።